የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ በኮሮናቫይረስ የተጠቁ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ቁጥር ማሻቀብ ከገደብ ለመላቀቂያ ዕቅዱ "ብርቱ" የኋሊዮሽ ምልሰት ነው ተባለ

*** ኒው ሳውዝ ዌይልስ ይዛ ከነበረው ዕቅድ አንድ ሳምንት ቀደም ብላ ትምህርት ቤቶችን ልትከፍት ነው

COVID-19 update

People are seen exercising along Southbank in Melbourne, Thursday, September 30, 2021. Source: AAP

  • ቪክቶሪያ የመጀመሪያ ዙር 80 ፐርሰንት የክትባት ዒላማዋን አለፈች
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ይዛ ከነበረው ዕቅድ አንድ ሳምንት ቀደም ብላ ትምህርት ቤቶችን ልትከፍት ነው
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከዕኩለ ለሊት በኋላ ሊረግብ ነው
  • ኩዊንስላንድ ስድስት ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስመዘገበች

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,438 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁት የአውስትራሊያ እግር ኳስ ሊግ የመጨረሻ ውድድር በተካሄደበት የሳምንቱ መጨረሻ ላይ በቡድን ከመሰባሰብ ጋር የተያያዘ ነው። የአምስት ሰዎች ሕይወትም አልፏል። 

ክስተቱን አስመልክቶ የቪክቶሪያ ኮቪድ-19 ኮማንደር ጄሮን ዌይማር ለቪክቶሪያ ከገደብ መውጪያ ዕቅድ "ብርቱ" የኋሊዮሽ ምልሰት እንደሆነ አበክረው ገልጠዋል። 

እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ቪክቶሪያ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በቂ የፋይዘር ክትባት አቅርቦት ስለሚኖራት በመጀመሪያና ሁለተኛ ክትባቶች መካከል የነበረውን የስድስት ሳምታት ክፍተት ወደ ሶስት ሳምንታት ዝቅ እንደሚል አስታውቀዋል።   

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 941 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን የሙዋዕለ ሕፃናት፣ አንደኛ ክፍልና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተያዘላቸው የትምህርት ቤት መመለሻ ጊዜ ቀደም ብለው ከኦክቶበር 18 ጀምሮ ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ይመለሳሉ።  

የተቀሩት ሌሎች ተማሪዎች ከሁለት ሳምንታት በኋላ ኦክቶበር 25 እና ኖቬምበር 1 ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ይመለሳሉ።  

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 31 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስመዘገበች።

ከዓርብ ኦክቶበር 12:01am ጀምሮ ከቤት ውጪ የመዝናኛ ሰዓታት ይራዘማሉ፣ ብሔራዊ ፓርኮች ይከፈታሉ፣ ለችርቻሮ ንግዶች ተጨማሪ ድጎማች ይደረጋሉ፣ ሌሎች ገደቦችም ይረግባሉ  

ዕድሜያቸው ከ60 በላይ ያሉ ነዋሪዎች የፋይዘር ክትባት መከተብ ይችላሉ።  

የኮቪድ-19  ክትባት ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ to                                                                                             

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • የ Brisbane, Gold Coast, Logan, Moreton Bay, Townsville እና Palm Island አካባቢ መንግሥታት ከዛሬ ሐሙስ 4pm ሴፕቴምበር 30 ጀምሮ የደረጃ 2 ገደቦች ተጥሎባቸዋል  
  • የፌዴራል መንግሥቱ ሥራቸውን ላጡ ሠራተኞችና ንግዶች ይሰጥ የነበረው የኮቪድ-19 አደጋ ድጎማ ሁለተኛ ዙር ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 80 ፐርሰንት ሲደርስ እንደሚያበቃ አስታወቀ።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 


Share
Published 30 September 2021 3:09pm
Updated 30 September 2021 3:13pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends