- የቪክቶሪያ መንግሥት የተወሰኑ አጣዳፊ ያልሆኑ ቀዶ ሕክምናዎች ከሰኞ አንስቶ እንደሚጀምሩ አስታውቋል። ሆኖም ሙሉ በሙሉ መቼ እንደሚጀምር አልተገለጠም።
- በሌላም በኩል የቪክቶሪያ መንግሥት ኦሚክሮንን ለመቋቋም የ$1.4 ቢሊየን የጤና ሥር ዓቱን ማጎልበቻ መመደቧን የክፍለ አገሪቱ ጤና ሚኒስትር ማርቲን ፎሊ ይፋ አድርገዋል።
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓታት 31 ነዋሪዎቿ በኮቪድ-19 ሕየወታቸውን ሲያጡ፤ ቪክቶሪያ 36 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት መድረጋቸውን አስመዝግባለች።
- የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት የክትባት መመዘኛዎችን ካሟሉ 170,000 የአረጋውያን ክብካቤ ነዋሪዎች ውስጥ 45,000 እስካሁን የሶስተኛ ዙር ኮቪድ-19 ክትባት እንዳልተከተቡ ተናገሩ።
- አቲ ሃንት በአረጋውያኑ ዘንድ ለሶስተኛ ዙር የኮቪድ-19 ክትባት ተከተባዎች ቁጥር ማነስ አንደኛው ምክንያት አመንቺነት መሆኑን ጠቁመዋል።
- የኩዊንስላንድ ዋና ጤና ኃላፊ ዶ/ር ጆን ጀራርድ የሶስተኛ ዙር ክትባት ያልተከተቡ አረጋውያን ሞት እንደሚያመዝን ገለጡ።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 10,698 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ31 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 2,494 ሕመማን 160 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ቪክቶሪያ ውስጥ 11,240 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 36 ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 707 ሕመማን 79 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ኩዊንስላንድ 6,857 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 13 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 732 ሕመማን 50 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ታዝማኒያ 570 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 13 ሕመማን 2 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 449 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል። ሆስፒታል ከሚገኙት 65 ሕመማን አንድ ግለሰብ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ይገኛል።
የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤
- ከ60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ዜናዎችና መረጃዎች ከ
- የክፍለ አገርዎ ረብ ያላቸው መምሪያዎች , , , , , , .
- ስለ ኮቪድ-19 መረጃ በቋንቋዎ