- ኩዊንስላንድ ውስጥ ዘጠኝ ሰዎች በኮቪድ-19 ተጠቅተዋል
- Cairns እና Yarrabah ከዛሬ 4pm ጀምሮ ገደብ ተጥሎባቸዋል
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 262 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል
- ቪክቶሪያ ውስጥ 11 ሰዎች ተጠቅተዋል
ኩዊንስላንድ
ኩዊንስላንድ በዛሬ ዕለት ዘጠኝ ሰዎች በቫይረስ የተጠቁባት መሆኑን አስመዝግባለች። ሰባቱ ከኢንዶርፖሊ፣ አንድ ከጎልድ ኮስት እና አንድ ከኬይንስ ናቸው።
ደቡብ-ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ እንደታሰበው ዛሬ 4pm ላይ ያበቃል፤ ይሁንና የፊት ጭምብል ማጥለቅን ጨምሮ የተወሰኑ ገደቦች ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ፀንተው ይቆያሉ።
የኩዊንስላንድ እንደራሴ አንስታዥያ ፓላሼ ኬይንስ ውስጥ በቫይረስ የተጠቃ አንድ የታክሲ ሾፌር ለ10 ቀናት ይሰራ የነበረ መሆኑ አሳሳቢ መሆኑን ገልጠዋል።
በዛም ሳቢያ የኬይንስ ሪጂናል ምክር ቤትና የያራባህ አቦርጂናል ሻየር ምክር ቤት ከዛሬ 4pm ጀምሮ ለሶስት ቀናት ገደብ ተጥሎባቸዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 262 ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙባት ሲሆን አንድ በ80ዎቹ የነበሩ አረጋዊት ሕይወታቸውን አጥተዋል።
72 ያህሉ በቫይረሱ የተጠቁት በማኅበረሰብ ተጋቦት ነው።
እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ፐንሪዝ ከተማ አካባቢ ያሉ 12 ክፍለ ከተሞች በስጋት አካባቢነት መመዝገባቸውንና ከእሑድ 5pm ጀምሮም ተጨማሪ ገደቦች የተጣሉባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬ ዕለት 11 ነዋሪዎቿ በኮቪድ-19 የተያዙ ሲሆን ሁሉም ቫይረሱ ከተዛመተባቸው አካባቢዎች ናቸው። በቫይረሱ በተጠቁበት ወቅት አንዳቸውም ወሸባ አልነበሩም።
ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 39 ያሉ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ከሰኞ ጀምሮ የአስትራዜኔካ ኮቪድ-19 ክትባትን በመጠነ ሰፊ የክትባት ማዕከላት መስጠት ይጀመራል።
አውስትራሊያ ውስጥ የመጀመሪያው የሆነው መኪና ውስጥ ሆኖ የክትባት መስጫ ማዕከል ከሰኞ ጀምሮ ሜልተን በሚገኘው የቀድሞው በኒንግስ መጋዘን ይከፈታል።
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤