የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስና ቪክቶሪያ ውስጥ በቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው

*** ቪክቶሪያ 1000 የጤና ሠራተኞችን ከባሕር ማዶ ልትመለምል ነው

COVID-19 update

Victorian Premier Daniel Andrews addresses the media during a press conference in Melbourne Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ለንግዱ ማኅበረሰብ የኮቪድ-19 ማቋቋሚያ ድጎማ መዘጋጀቱን አስታወቀች
  • ቪክቶሪያ መጠነ ሰፊ የጤና ክብካቤ ሙውዋዕለ ንዋይ ፍሰት ልታደርግ ነው
  • የጋራ ብልፅግናው በዓለም የመጀመሪያው የሆነ የልጆች የአዕምሮ ሕመም ዕቅድ መንደፉን አስታወቀ 

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1, 466 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የስምንት ሰዎች ሕይወትም አልፏል። ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እየተከታተሉ ካሉ 675 ሕሙማን ውስጥ ሙሉ ክትባት የተከተቡት ሰባት ፐርሰንት ብቻ ናቸው።
እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ከተቻላቸው የቪክቶሪ ነዋሪዎች የሁለትኛ ዙር ክትባት ቀነ ቀጠሯቸውን አሳጥረው አዲስ ቀጠሮ እንዲይዙ አሳስቡ። 

ቪክቶሪያ የጣለችውን ገደቦች ከማላላቷ በፊት የበርካታ ሚሊየን ዶላር ሙዋዕለ ንዋይ ፍሰት በጀት መመደቧን አስታወቀች።

የኮቪድ የመጀመሪያ ረድፍ ሆስፒታል ሠራተኞችን ለመደገፍ ከተመደበው $255 ሚሊየን ዶላር ውስጥ $2.5 ሚሊየኑ የሚውለው ባሕር ማዶ ያሉ 1000 የጤና ሠራተኞችን ለመመልመል ነው።

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
 ኒው ሳውዝ ዌይልስ 360 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

እንደራሴ ዶሚኒክ ፔሮቴይ ለክፍለ አገሩ የንግድ ማኅበረሰብ መርጃ የሚውል ድጎማ መመደቡን ገለጡ። 

የድጎማ መመዘኛዉን የሚያሟሉ ለተወሰኑ ግልጋሎቶችና ክፍያዎች ያዋሏቸውን ወጪዎች ተመርኩዘው $2,000 ተመላሽ መጠየቅ ይችላሉ። ለብልሽት ተዳራጊ ሸቀጦች ነጋዴዎችም ጠቀም ያለ ተመላሽ ድጎማ ከገና በዓል በፊት እንዲያገኙ ተመድቧል።

ይህንኑ አስመልክተው አቶ ፔሮቴይ “የንግድ ባለቤቶች የምንደግፋቸው መሆኑን ሊያውቁ ይገባል" ብለዋል። 

ኒው ሳውዝ ዌይልስ ሰኞ ዕለት ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ከ80 ፐርሰንት እንደሚያልፉ ይጠበቃል። 

Find a  near you.

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 28 ሰዎች በቫይረስ ተጠተዋል። ከታወቁ 22ቱ ቫይረሱ የተከሰቱባቸው ሥፍራዎች ነው።  

ዛሬውኑ የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

  • ኩዊንስላንድ ውስጥ አንድም ግለሰብ በቫይረስ አልተጠቃም።
  • የክትባት መመዘኛዎችን ከሚያሟሉ የአውስራሊያ ነዋሪዎች ውስጥ 82.8% የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ሲሆን 63.4% ሙሉ ክትባቶችን ተከትበዋል።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 


Share
Published 12 October 2021 6:02pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends