- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ወጣት ጎልማሶች ይበልጡን የቫይረስ ተጠቂዎች ናቸው
- ቪክቶሪያ በአምስት ሳምንታት ውስጥ አንድ ሚሊየን ሰዎችን ለመከተብ አቅዳለች
- በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ሁለት ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል
- ከአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ወደ ኩዊንስላንድ የሚጓዙ የግድ ወሸባ መግባት አለባቸው
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 390 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ 60 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል።
ዳቦና ዋልጌት ውስጥ አዲስ በቫይረስ ከተጠቁት 25 ሰዎች ሕፃናትን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ነባር ዜጎች ናቸው።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጤና ዲፓርትመንት ተወካይ ዶ/ር ሜሪአን ጌል ባለፉት ሁለት ሳምንታት በአብዛኛው በኮቪድ-19 የተጠቁት ዕድሜያቸው ከ 20-29 ያሉት እንደሆነ ጠቅሰው ክትባት እንዲከተቡም አሳስበዋል።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 15 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። አራቱ ቀደም ሲል ወረርሽኙ ተዛምቶባቸው ከነበሩ ሥፍራዎች አይደሉም።
እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ አስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሁሉ በእያንዳንዱ የቪክቶሪያ መንግሥት ክትባት ማዕከል እንደሚገኝና መንግሥት በሚቀጥሉት አምስት ሳምንታት ውስጥ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰዎች እንዲከተቡ የሚሻ መሆኑን ገልጡ።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ኩዊንስላንድ ሰባት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተውባታል። ከቅዳሜ ኦገስት 14 ጀምሮ ከአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ወደ ኩዊንስላንድ የሚጓዙ መንገደኞች የሆቴል ወሸባ ለመግባት ግድ ይሰኛሉ።
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ባለስልጣናት ከ 3,000 በላይ በቫይረስ ከተያዙ ሰዎች ጋር የቅርብ ንኪኪ ያላቸው ሆነው መገኘታቸውንና በጥቅሉ ስድስት ሰዎች በቫይረስ ተይዘው ያሉ መሆናቸውን አስታወቁ።
- የታዝማኒያ ንግዶች በወሰን መዘጋት ተጎድተዋል፤ በሌሎች ክፍለ አገራት ያሉ ከኦገስት 17 ጀምሮ ለድጎማ ማመልከት ይችላሉ።
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤