የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ የሲድኒ የጠበቁ ገደቦች ግብር ላይ ዋሉ

*** ኒው ሳውዝ ዌይልስ 818 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መጠቃታቸውንና የሶስት ሰዎች ሕይወትም ለሕልፈተ መዳረጉን አስታወቀች

COVID-19 update

Workers conduct a deep clean at Carlton Public School in Sydney, Monday, August 23, 2021. Source: AAP

  • ሲድኒ ውስጥ ኮሮናቫይረስ የተዛመተባቸው ሥፍራዎች ከ 9pm-5am የሰዓት እላፊና የአንድ ሰዓት አካላዊ እንቅስቃሴ ገደቦች ውጤት እየተመዘኑ ነው
  • ቪክቶሪያ 22 ለጊዜው ምንጫቸው ባልታወቀ ሁኔታ በቫይረስ የተጠቁ ሰዎችን አስመዝግባለች
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ዕድሜያቸው ከ16-29 ለሆኑት የፋይዘር ክትባት ምዝገባ ተከፈተ
  • ደቡብ አውስትራሊያ የቤት ውስጥ ወሸባ ሙከራ ጀመረች

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 818 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁባት መሆኑን በዛሬው ዕለት አስታወቀች፤ 42 በማኅበረሰብ ውስጥ የተዛመቱ ናቸው። የሶስት ሰዎች ሕይወትም አልፏል። ሟቾቹ በ80ዎቹ ውስጥ የነበሩና ስር የሰደደ ህመም የነበረባቸው ነበሩ። 

ከዛሬ ጀምሮ የካንተርበሪ ባንክስታውን፣ ካምበርላንድና ፌይርፊልድ ነዋሪ ሠራተኞች ከቀዬያቸው ውጪ ለሥራ በተሰማሩ ቁጥር የኮቪድ-19 ምርመራ አያሻቸውም   

የክትባትዎን ቀጠሮ ዛሬውኑ ይያዙ .

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 71ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 22ቱ ተስፋፍቶባቸው ካሉት ሥፍራዎች ጋር የተያያዙ አይደሉም። 55ቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።

ምንጩ ለጊዜው ያልታወቀ ቫይረስ Essendon West, Camberwell, Thornbury, Fitzroy North, Maidstone እና Sorrento ተከስቷል።

የመመርመሪያ ጣቢያዎችን ማወቅ ከፈለጉ ይህን ይጫኑ  በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከላትን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 16 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተተቅተዋል። ሶስቱ ገና በመጣራት ላይ ናቸው። ሶስቱ ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው።

ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 29 ያሉ የፋይዘር ኮቪድ-19 ክትባትን በ  ድረገጽ በኩል መመዝገብ ይችላሉ።

የመመርመሪያ ጣቢያዎችን ማወቅ ከፈለጉ ይህን ይጫኑ  ኮቪድ-19 ክትባት መሥፈርቱን የሚያሟሉ ስለመሆንዎ ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ .

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

Share
Published 23 August 2021 1:43pm
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends