የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ታምዎርዝ ላይ ገደብ ሲጣል፤ የሪጂናል ቪክቶሪያ ገደብ ይነሳል

*** ከማክሰኞ ኦገስት 10 ማለዳ 12:01am ጀምሮ ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ ይነሳል፤ የሜልበር ነዋሪዎች ያለ በቂ ምክንያት መሔድ አይችሉም።

COVID-19 vaccination

More than half of Australia's population aged 16 and above has received at least one dose of a coronavirus vaccine Source: AAP

  • ታምዎርዝ ላይ ገደብ ተጣለ፤ ባይሮን ቤይ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ይገኛል
  • የሪጂናል ቪክቶሪያ ገደብ ዛሬ እኩለ ለሊት ላይ ሊነሳ ነው
  • በአውስትራሊያ የመጀመሪያ የሆነው የሜልበርን የመኪና ውስጥ ክትባት ማዕከል ሥራ ጀመረ
  • ታዝማኒያ ውስጥ QR ኮድ ሥራ ላይ ሊውል ነው

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 283 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል። 64 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። 

ታምዎርዝ ላይ ከዛሬ 5pm ጀምሮ ለሰባት ቀናት ገደብ ተጥሏል፤ ከኒውካስል አንድ በቫይረስ የተጠቃ ሰው ወደ ሥፍራው ተጉዞ ስለነበር በርካታ የተጋላጭነት ሥፍራዎች ተለይተዋል  

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን አንድ ሰው በኮቪድ-19 በመጠቃቱ የተነሳ ሳቢያ በባይሮን ቤይ አካባቢ ተጨማሪ ምርመራዎች እንዲካሔዱ ጥሪ አቅርበዋል። 

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ .

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 11 ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል፤ ሁሉም ቫይረሱ ተከስቶ ካለባቸው አካባቢዎች ነው። 

እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ከማክሰኞ ኦገስት 10 ማለዳ 12:01am ጀምሮ ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ እንደሚነሳ አስታውቀዋል፤ የሜልበር ነዋሪዎች ያለ በቂ ምክንያት መሔድ እንደሌለባቸውም አስጠንቅቀዋል።

በአውስትራሊያ የመጀመሪያ የሆነው የሜልበርን የመኪና ውስጥ ክትባት ማዕከል በዛሬው ዕለት ሜልተን ውስጥ ሥራ ጀመሯል። 

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ .

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ኩዊንስላንድ አራት ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ መሆኑን አስመዘገበች። በደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ላይ የተጣሉ ገደቦችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ 
  • ኬይንስ እና ያራባህ ላይ የተጣለው ገደብ ረቡዕ ኦገስት 11 ያበቃል 
  • ታዝማኒያ ውስጥ ሁሉም የኡበርና ታክሲ ግልጋሎቶች ከዓርብ ኦገስት 13  ከምሽቱ 6 pm ጀምሮ QR ኮድ የመጠቀም ግዴታ ይኖርባቸዋል
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤



ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 


Share
Published 9 August 2021 3:18pm
By SBS/ALC Content
Source: SBS

Share this with family and friends