- ደቡብ አውስትራሊያ ወሰኖቿን ማክሰኞ ኖቬምበር 23 ክፍት ልታደርግ ነው። ይሁንና የክትባት መጠኑ ከ90 ፐርሰንት በታች ከሆነ የአካባቢ መንግሥታት ሥፍራ ወደ ክፍለ አገሪቱ የሚዘልቁ መንገደኞች እንደ hospice care እና Adelaide Ashes test ባሉ ከፍተኛ ተጋላጭነት ባላቸው ኩነቶች ላይ መገኘት አይፈቀድላቸውም።
- የቪክቶሪያ፣ ኒው ሳውዝ ዌይልስና የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ መንገደኞች በየ14 ቀናቱ በደቡብ አውስትራሊያ የስልክ አፕ የቫይረስ ምልክት መለያን መጠቀም ግድ ይሰኛሉ።
- የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፕሪሚየር ዲሴምበር 15 ቀሪ የኮሮናቫይረስ ገደቦች እንደሚነሱ አስታወቁ።
- ታዝማኒያ የዳንስና መጠጥ ኩነቶች፤ ቡና ቤቶችና ክለቦችን ከዲሴምበር 6 ጀምራ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ ሰዎች ክፍት እንደምታደርግ ገለጠች። ከፍለ አገሪቱ ወሰኗን ዲሴምበር 15 ክፍት ታደርጋለች።
- ታዝማኒያ ለታዳጊ ወጣቶች አይፎንና አይፓድ በመስጠት የክትባት መጠኗን ከፍ ለማድረግ የ5 ቀናት የክትባት ዘመቻ ታካሂዳለች።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,273 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ስምንት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 216 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መጠቃታቸውንና የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን አስታወቀች።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 17 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ ኖርዘርን ቴሪቶሪ ሁለት ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል።
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤