- የፈዋሽ ቁሶች አስተዳደር ኖቫቫክስ (Novavax) ኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ይሁንታውን ቸረ፤ አውስትራሊያ 51 ሚሊየን ኖቫቫክስ ክትባቶችን አዘዘች
- የፈዋሽ ቁሶች አስተዳደር በተጨማሪም ተጋላጭ ለሆኑ የኮቪድ ሕሙማን ለሚውሉ ሁለት የኪኒን ዓይንቶችም ይሁንታውን ቸሯል
- የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት ፓክስሎቪድና ሞልኑፒራቪር ኪኒኖች በመጪዎቹ ሳምንታት ወደ አውስትራሊያ እንደሚዘልቁ አስታውቀዋል
- በኮቪድ-19 ሳቢያ በመላው አውስትራሊያ የአርባ ዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ሆስፒታል ከሚገኙ 2,781 የኮቪድ ሕሙማን 212 በፅኑዕ ሕመምተኞች ክፍል ይገኛሉ
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 30,825 በቫይረስ ሲጠቁ 25 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል
- ኩዊንስላንድ ውስጥ ለሕልፈተ ሕይወት ከተዳረጉት ዘጠኝ ሰዎች ውስጥ አንዱ ስር የሰደደ ሕመም የነበረው የ 18 ዓመት ወጣት ሲሆን 16,812 በቫይረስ ተጠቅተዋል
የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 30,825 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ25 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
ቪክቶሪያ ውስጥ 20,769 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 18 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኩዊንስላንድ 16,812 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ ዘጠኝ ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።
ታዝማኒያ 927 ሰዎች ተጠቅቶባታል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 892 ሰዎች በቫይረስ መያዛቸውን አስመዝግባለች
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤
- ከ60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ዜናዎችና መረጃዎች ከ
- የክፍለ አገርዎ ረብ ያላቸው መምሪያዎች , , , , , , .
- ስለ ኮቪድ-19 መረጃ በቋንቋዎ