የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ በኮረናቫይረስ ከተጠቁት ሁለ ሶስተኛው ዕድሜያቸው ከ40 በታች ያሉ ናቸው

*** ቪክቶሪያ በፋይዘር ኮቪድ-19 የመጀመሪያና ሁለተኛ ክትባቶች መካከል ያለውን የጊዜ ገደብ ከሶስት ሳምንታት ወደ ስድስት ሳምንታት አራዘመች።

COVID-19 update

NSW police check identifications at George St in front of the Sydney Town Hall in anticipation of an anti-lockdown rally in Sydney. Source: AAP

  • በቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሲድኒ እንዳሻቀበ ነው
  • ቪክቶሪያ የፋይዘር ክትባት መከተቢያ ጊዜያትን አራዘመች
  • በደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ከዛሬ 4 pm ጀምሮ የአጭር ቀናት ገደብ ተጣለ
  • ታዝማኒያ ወሰኗን በኩዊንስላንድ ላይ ዘጋች

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 120 ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባትና የአንድ ሰው ሕይወትም ያለፈ መሆኑን አስታወቀች። ሕይወቱ ያለፈው ግለሰብ በስድሳዎቹ ዕድሜ ውስጥ የነበረና የደቡብ ምዕራብ ሲድኒ ነዋሪ ነበር።

የጤና ሚኒስትር ብራድ ሃዛርድ ሁለት-ሶስተኛዎቹ በቫይረስ የተጠቁት ሰዎች ዕድሜያቸው ከ40 በታች ያለና በፅኑ ሕመምተኞች ክፍል ሕክምና በመከታተል ውስጥ ካሉት ስድስቱ በሃያዎቹ ውስጥ ያሉ መሆናቸውን ገልጠዋል። 

የዴልታ ወረርሽኝ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ከጁን 16 አንስቶ መሰራጨት ከጀመረ ወዲህ 3190 በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ሁለት ነዋሪዎቿ  በቫይረስ የተጠቁባት መሆኑንና ሁለቱም ወሸባ ገብተው ያሉ መሆናቸውን አስታወቀች።

የቪክቶሪያ ጤና ሚኒስትር ማርቲን ፎሊ በፋይዘር ኮቪድ-19 የመጀመሪያና ሁለተኛ ክትባቶች መካከል የሚኖረው የጊዜ ገደብ ከሶስት ሳምንታት ወደ ስድስት ሳምንታት መራዘሙን ገለጡ።

ወቅታዊ የኮቪድ ጥንቃቄ እርምጃዎችን ከዚህ ያንብቡ .

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ 

  • ከስድስት ሰዎች በዴልታ ቫይረስ መጠቃት ጋር ተያይዞ  ከዛሬ 4pm ጀምሮ ለሶስት ቀናት የኮሮናቫይረስ ገደብ ተጥሎባቸዋል።
  • የአውስትራሊያ ሕክምና ማሕበር የአስትራዜኔካ ኮቪድ-19 ስጠ።
  • ታዝማኒያ በደቡ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ላይ ከዛሬ 4pm ጀምሮ ወሰኗን ዘጋች።

ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤



ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 

Share
Published 31 July 2021 3:18pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends