የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ዕድሜያቸው ከ5-11 ላሉ ልጆች ከጃኑዋሪ 10 ጀምሮ ክትባት ሊከተቡ ነው

*** የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የክትባቶች አቅርቦት በፋይዘር እስካልተረጋገጠ ድረስ የክትባት ቀነ - ቀጠሮ ምዝገባ እንደማትጀምር አስታወቀች።

COVID-19 update

PM Morrison met with the members of public in Sydney and made announcements regarding vaccination rollout for children. Source: AAP

  • ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን አውስትራሊያ ውስጥ 40 ሚሊየን ክትባቶች ጥቅም ላይ መዋላቸውን ገለጡ
  • አቶ ሞሪሰን አውስትራሊያ ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ካናዳና እንግሊዝ ስለ ልጆች ክትባት ተሞክሮዎች ልምድ መቅሰሟንም ተናግረዋል።
  • አውስትራሊያ ውስጥ ያሉ ዕድሜያቸው ከአምስት እስከ 11 ያሉ ልጆች ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ የፋይዘር ኮቪድ-19 ከትባት መከተብ ይጀምራሉ። የሞደርና ክትባትም ለክትባትነት እንዲውል ይሁንታ ተጠይቋል።  
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለፉት 24 ሰዓታት አንድም በኦሚክሮን የተጠቃ ግለሰብ አላስመዘገበችም፤ ይሁንና ሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ የውኃ ፍሳሽ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ናሙና ተገኝቷል።
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የክትባቶች አቅርቦት በፋይዘር እስካልተረጋገጠ ድረስ የክትባት ቀነ - ቀጠሮ ምዝገባ እንደማትጀምር አስታወቀች።

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ቪክቶሪያ ውስጥ  1,206 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 516 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቅተዋል። 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ስድስት፤ ኩዊንስላንድ አራት ነዋሪዎቻቸው በቫይረስ መጠቃታቸውን አስመዝግበዋል።  

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

 የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ 

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  


 

 


Share
Published 10 December 2021 4:43pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends