የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ - ቪክቶሪያና ኩዊንስላንድ የኮሮናቫይረስ ገደቦች ድንጋጌዎች ላይ ለውጥ አደረጉ

*** ቪክቶሪያ ከፌብሪዋሪ 25 ጀምሮ ኩዊንስላንድ ከማርች 4 ጀምሮ የፊት ጭምብል የማጥለቅ ድንጋጌዎች ይነሳሉ

COVID-19 update

Face mask mandates are changing in Australia. Different rules apply in different States and Territories. Source: AAP

  • ኩዊንስላንድ ከማርች 4 ከምሽቱ 6pm ጀምሮ ከተወሰኑ ሥፍራዎች በስተቀር የፊት ጭምብል የማጥለቅ ድንጋጌን አንስታለች። የፊት ጭምብል ማጥለቅ ግዴታ ረግቶ የሚቆይባቸው ሥፍራዎች ሆስፒታል፣ የአረጋውያን ክብካቤ ተቋማት፣ የግብረ አካል ጉዳተኞች መኖሪያዎች፣ እሥር ቤቶች፣ አውሮፕላን ማረፊያዎች፣ የሕዝብ ትራንስፖርትና አውሮፕላኖች ይሆናሉ። 
  • ከዚያው ቀን ጀምሮ የተለያዩ ኩነት ተስተናጋጆች ቁጥር መጠን ገደቦች ይነሳሉ። 
  • ከማርች ወር ጀምሮ ዕለታዊ የኮቪድ-19 ጋዜጣዊ መግለጫ አይካሄድም። 
  • ቪክቶሪያ በሕዝብ ጤና ምክረ ሃሳብ መሠረት ከዓርብ ፌብሪዋሪ 25 ከምሽቱ 11.59pm አንስቶ አብዛኛዎቹ የፊት ጭምብል የማጥለቅ ድንጋጌዎች ይነሳሉ፤ ከቤት ሆኖ መሥራትና መማር የተገታ ይሆናል። 
  • ቪክቶሪያ ውስጥ በሕዝብ ትራንስፖርት፣ ታክሲዎች፣ አውሮፕላን ውስጥና አውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ሆስፒታልና የክብካቤ ተቋማት ውስጥ የፊት ጭምብልን የማጥለቅ ግዴታ ይቀጥላል። 
  • ቪክቶሪያ ዕድሜያቸው ከ5 እስከ 11 ያሉ ልጆች የክትባት መጠን ዝቅተኛ መሆንን ተከትሎ የሙዋዕለ ሕፃናት ሠራተኞችና ከ3ኛ ከፍል ጀምሮ ያሉ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ መምሕራንና ሠራተኞች የፊት ጭምብል የማጥለቅ ግዴታ ይኖርባቸዋል። በሁለተኛ ደረጃ ላሉ የፊት ጭምብልን ማጥለቅ አማራጭ ይሆናል። 
  • ቪክቶሪያ ውስጥ በመስተንግዶ፣ የችርቻሮ፣ የፍትሕና የማረሚያ ተቋማት ሥፍራዎች የፊት ጭምብል ማጥለቅ ግድ ይላል።
  • ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የቪክቶሪያ ሆስፒታሎች አጣዳፊ ያልሆኑ የቀዶ ሕክምና ግልጋሎቶች ይጀምራሉ።
  • የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ቁጥር በ90 ፐርሰንት መቀነሱን ገለጡ። 
  • የሆስፒታል ህሙማን ቁጥር በግማሽ መቀነሱም አቶ ሃንት ተናግረዋል። 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 8,752 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ14 ሰዎች ሕይወት አልፏል። ሆስፒታል ከሚገኙት 1,293 ሕመማን 71 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ቪክቶሪያ ውስጥ 6,786  በቫይረስ ሲጠቁ፤ 14 ሕይወታቸውን አጥተዋል።  ሆስፒታል ከሚገኙት 345 ሕመማን 8 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች  በአየር መተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ። 

ኩዊንስላንድ 5,583 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 5 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 394 ሕመማን 34 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።  

ታዝማኒያ 820 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 11 ሕሙማን መካክል ሁለት ግለሰቦች በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ይገኛሉ።

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 583  ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 41 ሕመማን 1 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ይገኛል።  

 



 

 



 

Find a COVID-19 testing clinic

 

 

 



 

Register your RAT results here, if you're positive 

 

 

 



 

Find out  anywhere in Australia

 

If you need financial assistance, 

 

Here is some help understanding 

 



 

Read all COVID-19 information in your language on the.

 

 



Share
Published 22 February 2022 8:02pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends