የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ቪክቶሪያ የኮሮናቫይረስ ገደብ ጣለች

*** ቪክቶሪያ በኮቪድ - 19 ስምንት ሰዎች ተጠቅተውባታል፤ ገደቡ ከዛሬ ምሽት 8 pm ጀምሮ የፀና ይሆናል

COVID-19 update

Victorian Premier Daniel Andrews. Source: AAP

ከዛሬ ሐሙስ ኦገስት 5 ጀምሮ ለሰባት ቀናት ፀንቶ የሚቆይ የኮሮናቫይረስ ገደብ ቪክቶሪያ ላይ መጣሉን እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ አስታወቁ።

በዚህም መሠረት፤

ማኅበራዊ


ከቤትዎ መውጣት የሚችሉት ለአምስት ጉዳዮች ብቻ ይሆናል።
  • መሠረታዊ ለሆኑ የገበያ ሸመታ
  • ለሌሎች ክብካቤ ለማድረግ
  • ፈቃድ ያለው የሥራ ገበታ ላይ ለመሠማራት
  • እስከ ሁለት ሰዓት የሚደርስ የአካል እንቅስቃሴ ለማድረግ (ከሁለት ሰው በላይ አይፈቀደም) 
  • ክትባት ለመከተብና ልዩ ፈቃድ ሲኖር ይሆናል።
  • ፍቅራዊ ግንኙነት ካለዎት ግለሰብ በስተቀር ቤትዎ ውስጥ ጎብኚዎች ማስተናገድ አይችሉም።
  • በግልና በአደባባይ መሰባሰብ አይፈቀደም።
  • ከቤት ሆነው መሥራት የሚችሉ ከሆነ ሥራዎን ቤትዎ ሆነው ማከናወን ይችላሉ።

 
የ5 ኪሎ ሜትሮች ገደብ
ከመኖሪያ ቤትዎ ርቀው መሔድ የሚችሉ እስከ 5 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ብቻ ነው። 

ከተፈቀደልዎት የርቀት ገደብ ውጪ መሔድ የሚችሉት፤

  • በ5 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ውስጥ አስፈላጊዎ የሆኑ ቁሳቁሶችን ለመሸመት ወይም ግልጋሎቶችን ለመጠቀም የማይችሉ ከሆነ
  • ፍቅረኛዎን ለመጎብኘት
  • ፈቃድ ያለዎት ሠራተኛ ከሆኑ
  • ክብካቤ ለማድረግና ሌሎች ሰብዓዊ ርህራሄን ግድ የሚሉ ጉዳዮች ካለዎት ይሆናል።

የፊት ጭምብሎች

ቤትዎ ውስጥ ካልሆነና ከጤና ጋር የተያያዘ ፈቃድ ከሌለዎት በስተቀር በማናቸውም የቤት ውስጥና ከቤት ውጪ እንቅስቃሴዎ ወቅት የፊት ጭምብሎችን የማድረግ ግዴታ አለብዎት።


ትምህርትና ሙዋዕለ ሕጻናት
ሙዋዕለ ሕጻናትና የቤተሰብና ሕጻናት ክብካቤ ማዕከላት ክፍት ይሆናሉ።

ትምህርት ቤቶች ተጋላጭ ከሆኑና በሥራ ገበታቸው ላይ መገኘት እጅጉ አስፈላጊ ከሆኑ ሠራተኞች ልጆች በስተቀር የትምህርት አሰጣጣቸው በርቀት የማስተማሪያ ዘዴ ይሆናል።

የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የርቀት ትምህርት ብቻ ይሰጣሉ።

ችርቻሮ


የምግብና መስተንግዶ ግልጋሎት ሰጪዎች ግልጋሎቶቻቸውን አዝዘው ወደ ቤታቸው በሚወስዱ ደንበኞች ብቻ ይወሰናል።
ግልጋሎቶቻቸው በእጅጉ አስፈላጊ የሆኑ ቸርቻሪዎች ለአንድ ሰው በ 4 ስኩየር ሜትር ርቀት ገደብ አገልግሎቶቻቸውን ለመስጠት ክፍት ይሆናሉ።
ሌሎች ቸርቻሪዎች በኦንላይን አዝዘው ንክኪ በሌለው መንገድ ግልጋሎቶቻቸውን መጥተው ለሚወስዱ ደንበኞች አገልግሎቶቻቸውን መስጠት ይችላሉ። 
ጸጉር ማስተካካከያ፣ የውበት ሳሎንና የግላዊ ክብካቤ ንግድ ቤቶች ዝግ ይሆናሉ። 
አካላዊ እንቃስቃሴ ማካሄጃ


የቤት ውስጥ አካላዊ መዝናኛዎችና የስፖርት እንቅስቃሴዎች ዝግ ይሆናሉ።

ከቤት ውጪ አካላዊ መዝናኛና የስፖርት እንቅስቃሴዎች የተከለከሉ ሆነው የመጫዎቻ ሥፍራዎች ክፍት ይሆናሉ።

ኩነቶች


የሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ላይ በኦንላይን ካልሆነ በስተቀር በአካል መታደም የተከለከለ ነው።



 


Share
Published 5 August 2021 5:51pm
Updated 5 August 2021 5:57pm
By Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends