- የኩዊንስላንድ ፕሪሚየር አናስታዥያ ፓለሼይ በኩዊንስላንድና ኒው ሳውዝ ዌይልስ ወካከል ያሉትን ወሰኖች ለመክፈት ክለሳ እንደሚያደርጉ ገለጡ።
- የኖርዘርን ቴሪቶሪ ዋና ሚኒስትር ማይክል ጋነር ነዋሪዎች ከባሕር ማዶኞች አሳሳች መረጃ ይልቅ የአረጋውያንን ምክሮች እንዲከተሉ አሳሰቡ።
- ቪክቶሪያ ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ነዋሪዎች የክትባት ቁጥር 90 ፐርሰንት መድረሱን ተከትሎ የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ ችርቻሮና ግልጋሎት ሰጪዎች የኮቪድ-19 ፕሮቶኮሎችን ከማስፈጸም ቸል እንዳይሉ አሳሰቡ።
- የኮሮናቫይረስ ተስፋፍቶባት ካለችው ከካትሪን የአካባቢ መንግሥት ወደ ደቡብ አውስትራሊያ የሚጓዙ መንገደኞች በ 'ከፍተኛ ተጋላጭነት' በመፈረጇ ለሰባት ቀናት ወሸባ መግባት ግድ ይሰኛሉ።
- በዓለም አቀፍ ድንበሮች መዘጋት ሳቢያ የጊዜያዊ ምሩቃን (ንዑስ መደብ 485) ቪዛ ባለቤቶች ሆነው ወደ አውስትራሊያ መምጣት ያልቻሉ ለቀድሞ ቪዛቸው መተኪያ ማመለክት ይችላሉ .
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,254 በቫይረስ ሲጠቁ፤ አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 276 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ጠቅተዋል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ ስምንት ሰዎች፤ ኖርዘን ቴሪቶሪ ውስጥ አንድ ግለሰብ በቫይረስ ተይዘዋል።
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤