- ቪክቶሪያ ማሕበረሰባት ወሰን ተሻግረው እንዲገናኙ ልታደርግ ነው
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ሁሉም ሰው የኮቪድ ጥንቃቄ ባህሪይን ጠብቆ እንዲቀጥል አሳሰበች
- ከ 68 ፐርሰንት የካንብራ ነዋሪዎች ሙሉ ክትባት ተከትበዋል
- ኩዊንስላንድና ደቡብ አውስትራሊያ ገደቦቻቸውን አረገቡ
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,838 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የአምስት ሰዎች ሕይወትም አልፏል።
በርካታ የአካባቢ መንግሥታት Benalla, Greater Bendigo, Buloke Shire, Loddon, Yarriambiack, Hay, Edward River, Lockhart, Murrumbidgee, Wagga Waggaን ጨምሮ ወሰን መሻገር ሊጀምሩ ነው።
ባለፉት 14 ቀን በእነዚህ አካባቢ መንግሥት ቆይተው ያሉ ነዋሪዎች ያለ ምንም ፈቃድ ቪክቶሪያን ለቅቀው መውጣት ወይም መግባት ይችላሉ።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 646 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 11 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። እስካሁን ከኮቪድ ጋር በተያያዘ የ414 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
በምዕራብ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ሃንተር ኒው ኢንግላንድ ዊ ዋ፣ ኩዪሪንዲ እና ብሪዋሪና የፍሳሽ ቁሻሻ ውስጥ ቫይረስ ተገኝቷል።
ዋና የጤና መኮንን ዶ/ር ኬሪ ቻንት ነዋሪዎች በሙሉ የፊት ጭምብል ማጥለቅ፣ QR ኮድ መጠቀም፣ ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅና ከሁሉም በላይ የኮቪድ-19 ምልክቶች የተሰማው ግለሰብ ምርመራ ማካሄድና ራስን ማግለልን መተግበር እንደሚያሻ አስታውቀዋል።
ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ቴሪቶሪ ካፒታል ውስጥ 40 ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል።
በአሁኑ ወቅት ሆስፒታል ውስጥ 16 በሽተኞች ያሉ ሲሆን ስድስቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል አምስት በመተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ከዛሬ ዓርብ ኦክቶበር 8 ከቀትር በኋላ 4pm አንስቶ የBrisbane, Logan, Gold Coast, Moreton Bay, Townsville (including Magnetic Island), እና Palm Island ደረጃ 3 ገደቦች ላይ ካለው የተቀረው የኩዊንስላንድ አካባቢ መንግሥታት ጋር ይገጥማሉ
- የደቡብ አውስትራሊያ ደቡብ ምሥራቅ በተቀረው ክፍለ አገር ላይ ተጥለው ካሉት ደረጃ 1 ገደቦች ስር ተጠቃለለ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤