- ቪክቶሪያ ውስጥ 1,220 ሰዎች በቫይረስ ተጠቁ
- የኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለ ስልጣናት ነዋሪዎች የብሔራዊ ራግቢ ሊግ ውድድርን ለመመልከት ሲሉ የመሰብሰብ የጤና ደንቦችን እንዳይጥሱ አሳሰቡ
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 38 ነዋሪዎች በቫይረስ ተያዙ
- ታዝማኒያ አንድ ነዋሪዋ በቫይረስ መጠቃቱን አስመዘገበች
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,220 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የሁለት ሰዎች ሕይወትም አልፏል።
እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ የገደቦች መጣል የጤና ሥር ዓቱን ለማስጠበቅና የጤና ባለ ሙያተኞችን ለማክበር እንደሆነ አመላክተው " ለእኛ ነፃነት ማለት ለጤና ሥርዓታችን የከፋ ጊዜ ይሆናል" ብለዋል።
ትናንትና ፖሊስ ሜልበርን ውስጥ የፀረ ክትባት ተቃውሞ ሲያካሂዱ የነበሩ 109 ሰዎችን ዘብጥያ አውርዷል።
በሮያል ሜልበርን ሆስፒታል የፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ነርስ ሥራ አስኪያጅ ሚሼል ስፔንስ ከወርኃ ጁላይ አንስቶ እስካሁን የፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ 90 ሰዎች አንዳቸውም ክትባት ያልተከተቡ መሆናቸው ገለጡ።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 667 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 10 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ሲድኒ ላይ የኮሮናቫይረስ ገደቦች ከተጣሉ 100 ቀናት ተቆጠረ።
የጤና ሚኒስትር ብራድ ሃዛርድ የብሔራዊ ራግቢ ሊግ የፍጻሜ ውድድር ግጥሚያን ክመመልክት ጋር ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲያሳስቡ "ቤታችሁ ቫይረስ ከማስተላለፍ ረገድ አንዱና ዋነኛ አደገኛ ሥፍራ ሆኖ የሚቆይ ነው" ብለዋል።
ከኦክቶበር 11 ጀምሮ ክትባት የተከተቡ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች በቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንኪኪ በሚገጥማቸው ወቅት ለ14 ቀናት ራሳቸውን ከማግለል ይልቅ ለ 7 ቀናት ብቻ ወሸባ ይገባሉ።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 38 ነዋሪዎች በቫይረስ መያዛቸውን አስመዘገበች። 16ቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
- ከሜልበርን ወደ ሎንሴስተን በአውሮፕላን የተጓዘ አንድ ታዳጊ ወጣት በኮቪድ-19 ተይዟል።
- ኩዊንስላንድ ውስጥ አንድም ሰው በቫይረስ አልተያዘም። በፐንሪዝ ፓንዘርስ እና ደቡብ ሲድኒ ራቢቶስ ቡድናት መካከል የሚካሄደው የብሔራዊ ራግቢ ሊግ የፍፃሜ ግጥሚያ ዛሬ ምሽት በብሪስበን ላንግ ፓርክ ስታዲየም ይካሄዳል።
- ደቡብ አውስትራሊያ ትናንት ከቀትር በኋላ ሁለት ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስታወቀች።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤