- ቪክቶሪያ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ከአገረሸ ወዲህ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር አስመዘገበች
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዚህ ሳምንት መጨረሻ የሙሉ ተከታቢ ነዋሪዎቿ ብዛት 80 ፐርሰንት ሊደርስ ነው
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተጋላጭነት ሥፍራዎች ተመዘገቡ
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1, 571 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 13 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
የሜልበርን ሮያል ሕፃናት ሆስፒታል ለሕመምተኛ ጠያቂ ወላጆች ፈጣን የኪቪድ መመርመሪያ ሥራ ላይ ሊያውል ነው።
ዛሬ ምሽት ላይ በሂዩም ሪጅን ሚችል ሻየር ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ እንደሚነሳ የቪክቶሪያ ጤና ሚኒስትር አስታወቁ።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 444 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አራት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
እሑድ ዕለት ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 80 ፐርሰንት እንደሚደርስ ይጠበቃል።
እንደራሴ ዶሚኒክ ፔሮቴይ በነገው ዕለት በሚያካሂዱት የካቢኔ ስብሰባ ላይ በሚቀጥለው ሳምንት የሚረግቡትን ገደቦች አስመልክቶ የፍኖተ ካርታ ማሻሻያ ሊደረግ እንደሚችል አመላከቱ። የገደቦች ማሻሻያውን አስመልክቶም ዓርብ ዕለት መግለጫ ይሰጥበታል።
ዕድሜያቸው ከ16 በላይ ከሆኑ ነዋሪዎች ውስጥ 75.2 ፐርሰንት ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሲሆን 90 ፐርሰንቱ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከትበዋል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 51 ሰዎች በቫይረስ ተጠተዋል። ሆስፒታል ህክምና እያገኙ ካሉት 16 ሕሙማን ውስጥ ስምንቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች የሚገኙ ሲሆን አምስቱ በመተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።
በአሁኑ ወቅት 370 የተጋላጭነት ሥፍራዎች ያሉ ሲሆን የካንብራ ነዋሪዎች አዲሶቹን የተጋላጭነት ሥፍራዎች እንዲለዩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ቪክቶሪያ እየበረከተ የመጣውን የቫይረስ ሕሙማን ቁጥር ለመቋቋም ከባሕር ማዶ 1000 የጤና ክብካቤ ሠራተኞችን ልታስመጣ ነው።
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከዓለም በብዛት የተከተቡ ነዋሪዎች ካሏቸው ከተሞች አንዷ ሆናለች፤ በወርኃ ኖቬምበር መጨረሻ 99 ፐርሰንት ነዋሪዎቿ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።