- ክቶሪያ ውስጥ 1,488 ሰዎች በቫይረስ ተጠቁ
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 813 በቫይረስ ተያዙ
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 52 ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል
- ኩዊንስላንድ ወሸባ ያሉ ሁለት ሰዎች በቫይረስ መጠቃታቸውን አስመዘገበች
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,488 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የሁለት ሰዎች ሕይወትም አልፏል። የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከፍተኛው ዕለታዊ አኃዝ ሆኖ ተመዝግቧል። በአሁኑ ወቅት 429 ሰዎች የሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ ሲሆን 97ቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል 54ቱ በመተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።
በርካታ የሕክምና ተቋማት ዋራንቡል፣ ሼፐርተን፣ ጊስቦርን፣ ኢስት ቤንዲጎ፣ ሙካታህ እና ባላራትን ጨምሮ የቪክቶሪያ ከፍተኛ ኮቪድ ተጋላጭነት ሥፍራዎች ውስጥ የሚገኙ ናቸው
በጅሮንድ ቲም ፓላስ የግለሰብ ንግዶችን ጨምሮ መመዘኛ ለሚያሟሉ ንግዶች የአንድ ጊዜ ክፍያ ድጎማ የሚውል $196.6 ሚሊየን መመደቡን አስታወቁ። ድጎማው ያስፈለገው ከሴፕቴምበር 21 እስከ ኦክቶበር 4 ከተጣሉ ገደቦች ጋር ተያይዞ ነው።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 831 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 10 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 1,005 ሰዎች የሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ሲሆን 202ቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል 99ኙ በመተፈንሻ መሳሪያ እየተረዱ ናቸው።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጤና ተወካይ ዶ/ር ጀርሚ ማክአኑልቲ በዚህ ሳምንት መጨረሻ እሑድ ዕለት ብሪስበን የሚካሔደውን የብሔራዊ ራግቢ ሊግ የመጨረሻ ውድድር ለመመልከት ነዋሪዎች ከጤና መመሪያዎች ውጪ በየግል መኖሪያ ቤቶች ውስጥ እንዳይሰባሰቡ አሳስበዋል።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 52 ሰዎች በኮቪድ-19 ተጠቅተዋል፤ 29ኙ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
- የኩዊንስላንድ ባለስልጣናት ወሸባ ውስጥ የነበሩ ሁለት ልጆች በብሪስበን አቬይሽን ከተከሰተው ቫይረስ ጋር በተያያዘ መጠቃታቸውን አስታወቁ።
- የኩዊንስላንድ ጤና ሚኒስትር ኢቬት ዳት ነገ የብሔራዊ ራግቢ ሊግ የመጨረሻ ግጥሚያ በሚካሔድበት ስታዲየም ዙሪያ ተንቀሳቃሽ የክትባት ክሊኒኮች እንደሚቆሙ ገለጡ።

Source: SBS
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤