የኮቪድ - 19- ወቅታዊ መረጃ ቪክቶሪያ የግንባታ ስፍራዎችን ክፍት ልታደርግ ነው ፤ በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከፍተኛ የተባለው የኮሮናቫይረስ ቁጥር ተመዘገበ

ይህ በአውስትራሊያ ኦክቶበር 10 , 2020 የተሻሻለ የኮሮናቫይረስ መረጃ ነው፡፡

Victoria announces vaccine mandate for authorised workers

Victoria announces vaccine mandate for authorised workers Source: AAP Image/Lukas Coch

Victoria vs NSW case numbers
Source: SBS
  • ቪክቶሪያ ፈቃድ ያላቸው ሰራተኞች ክትባትን የግድ መውሰድ እንዳለባቸው አስታወቀች
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ  የንግድ ተቋማት የገንዘብ ድጎማን ማግኘታቸው ይቀጥላል ተባለ
  • ኩዊንስላንድ ሁለት ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስታወቀች
 ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,143 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤

ፈቃድ ያላቸው ሰራተኞች በሙሉ በስራቸው ላይ መቀጠል ከፈለጉ፤፤ እስከ ኦክቶበር 15 ድርስ ቢያንስ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ማግኘት አለባቸው ፡፡ በተያያዘም እስከ ኖቬምበር 26 ድረስ ሙሉ ለሙሉ መከተብ ይኖርባቸዋል ፡፡

ከማክሰኞ ኦክቶበር 5 ጀምሮ 25 በመቶ የሚሆኑት የግንባታ ሰራ ባላሙያዎች ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሳሉ ፡፡ ይሁንና ሰራተኞቹ ቢያንስ አንዱን ዙር ክትባት መውሰድ አለባቸው ፡፡

የሞራቦል ሎካል ገቨርንመንት አካባቢ ከዛሬ እኩለ ለሊት በኋላ ለሰባት ቀናት በሚቆይ ገደብ ውስጥ ይቆያሉ ፡፡

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

ኒው ሳውዝ ዌይልስ  

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 864 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን 15 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

አቃቤ ነዋይ ዶምኒክ ፔሮቴት እንዳረጋገጡት ከሆነ የንግድ ተቋማት የተቀመጠውን መስፈርት እስካሟሉ ድረስ የገንዘብ ድጎማን እስከ ኖቬምበር 30 ድረስ ያገኛሉ ፡፡

ለጥቃቅን የንግድ ተቋማት የሚሰጠው የገንዘብ ድጎማም የሚቀጥል ሲሆን ትርፋቸው ከ $75,000 በታች ለሆኑት ተቋማት ድጎማው ቀንሶ በሁለት ሳምንት ወደ $750 ዝቅ ይላል ፡፡

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 53  ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተያዙ ሲሆን የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከፍተኛ ሚኒስትር አንድው ባር እንዳሉት 40 በመቶ የሚሆኑ እና መከተብ የሚገባቸው የክንብራ ነዋሪዎች ክትባቱን አልወሰዱም ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አብዛኛዎች ከ 40 አመት በታች ናቸው፡፡

የኮቪድ-19  ክትባት ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ to                                                                                             

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ACT  and 
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

 
 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 

 


Share
Published 1 October 2021 4:01pm
By SBS/ALC Content
Presented by Martha Tsegaw
Source: SBS


Share this with family and friends