ቪክቶሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፈጣን የኮሮናቫይረስ መመርመሪያዎችን ልትገዛ ነው

*** ዕድሜያቸው ከ12 በላይ የሆኑ የካንብራ ነዋሪዎች ከ 66 ፐርሰንት በላይ ሙሉ ክትባት ተከትበዋል

COVID-19 update

Victorian Health Minister Martin Foley (left) and Victorian COVID-19 Commander Jeroen Weimar in Melbourne, Wednesday, October 6, 2021. Source: AAP

  • ቪክቶሪያ 2.2 ሚሊየን ፈጣን የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ልትገዛ ነው
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ለንግድ ማኅበረሰብ አዲስ የፋይናንስ እክል መደጎሚያ ሥርዓት አበጀች
  • ዕድሜያቸው ከ12 በላይ የሆኑ የካንብራ ነዋሪዎች ከ 66 ፐርሰንት በላይ ሙሉ ክትባት ተከትበዋል
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ አንድም ሰው በቫይረስ አልተያዘም

ቪክቶሪያ
 ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,420 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የአስራ አንድ ሰዎች ሕይወትም አልፏል። በቅርቡ ከተከሰተው ወረርሽኝ ወዲህ ለሞት የዳረጉ ሰዎች ቁጥር 68 ደርሷል።   

የቪክቶሪያ መንግሥት 2.2 ሚሊየን ፈጣን antigen መመርመሪያዎችን ሊገዛ ነው። ጥቅም ላይ የሚውለውም በቅድሚያ በጤና ክብካቤ ሥርዓቱ በኩል ሲሆን ቀጥሎም ለትምህርት ቤቶችና የድንገተኛ አደጋ ግልጋሎት ሰጪዎችን ለመሳሰሉቱ ይዳረሳል።

የጤና ሚኒስትር ማርቲን ፎሊ 90,000 የቪክቶሪያ ነዋሪዎች በትናንትናው ዕለት እንደተከተቡና ያም ማክሰኞ ኦክቶበር 5 በአገር አቀፍ ደረጃ ከተከፋፈለው ከግማሽ በላይ መሆኑን ገልጠዋል። 

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 594 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አሥር ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

ለኮቪድ-19 የንግድ ድጋፍ መመዘኛዎችን ለማያሟሉና ለፋይናንስ እክል ለተዳረጉ ንግዶች መርጃ የሚውል አዲስ የክለሳ ቡድን ተመሥርቷል  

ቡድኑ የ2021 ኮቪድ-19 የንግድ ድጋፍ መመዘኛዎችን የማያሟሉ ንግዶችን ጉዳይ ፈርጅ በፈርጅ ይመለከታል።

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

የአውስትራሊያ ቴሪቶሪ ካፒታል ውስጥ 28 ሰዎች በቫይረስ ሲያዙ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል። 

አንድ ጨቅላ ሕፃን በቫይረስ ተይዞ በካንተርበሪ የሴቶችና ሕፃናት ሆስፒታል ውስጥ የሕክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል። 

እስካሁን ድረስ የአውስትራሊያ ቴሪቶሪ ካፒታል ውስጥ 395 ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል። 

የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • እንደራሴ አንስቴዥይ ፓለሼይ የመጀሪያ ዙር ክትብት የተከተቡ የብሪስበን ነዋሪዎች 70 ፐርሰንት ለመድረስ መቃረብን ተከትሎ የኢፒስዊች፣ ሎጋን፣ ቢዩደዘርትን ሰንሻይን ኮስት ነዋሪዎች ክትባት እንዲከተቡ ኣሳሰቡ።
 

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 

Share
Published 6 October 2021 3:34pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends