እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ የቪክቶሪያን ከኮሮናቫይረስ ገደቦች መውጫ ፍኖተ ካርታ ዛሬ እሑድ ሴፕቴምበር 19 ይፋ አድርገዋል።
ፍኖተ ካርታውን ግብር ላይ ለማዋል እንደታሰበው ኦክቶበር 26 የክትባት መመዘኛዎችን ከሚያሟሉት ውስጥ 70 ፐርሰንት የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ሙሉ ክትባት ከተከትቡ ተጥለው ያሉ ገደቦች እንዲያከትሙ ይደረጋል።
በዚህም መሠረት፤
ማኅበራዊ
- የሰዓት ዕላፊን ጨምሮ ተጥለው ያሉ ገደቦች ኦክቶበር 26 ይነሳሉ
- ሙሉ ክትባት የተከተቡ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች 70 ፐርሰንት ሲደርስ የጉዞ ገደብ አይኖርም፤ እስከ 50 ሰዎች ከቤት ውጪ መሰባሰብ ይችላሉ
- የተከታቢዎች ቁጥር 80 ፐርሰንት ሲደርስ ከ10 ያልበለጡ ሰዎች ቤትዎ መጥተው ሊጎበኝዎት ይችላሉ
- የተከታቢዎች ቁጥር 80 ፐርሰንት ከደረሰ የገና ዕለት ከ30 ያልበለጡ እንግዶችን ቤትዎ ውስጥ ማስተናገድ ይችላሉ
የፊት ጭምብሎች
- የፊት ጭምብሎችን ማጥለቅ ለጊዜው ይቀጥላል
- ነዋሪዎች 80 ፐርሰንት ሙሉ ክትባት ሲከተቡ ከቤት ውስጥ በስተቀር የፊት ጭምብሎችን ማጥለቅ ግድ አይሰኙም
መስተንግዶዎች - ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ሙሉ የክትባት ደረጃ 70 ፐርሰንት ሲደርስ
- ቡና ቤቶች፣ ክለብና መዝናኛዎች የርቀት መጠንን ጠብቆ ከ50 ያልበለጡ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ደንበኞችን ከቤት ውጪ ማስተናገድ ይችላሉ
- የፀጉርና የውበት ሳሎን የርቀት መጠንን ጠብቆ ከ5 ያልበለጡ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ደንበኞችን ማስተናገድ ይችላሉ
- የማኅበረሰብ ስፖርቶች ይጀምራሉ
መስተንግዶዎች - ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ሙሉ የክትባት ደረጃ 80 ፐርሰንት ሲደርስ
-
የመስተንግዶ፣ ችርቻሮና መዝናኛ ግልጋሎት ሰጪዎች ጥብቅ የሆነ የርቀት መጠንን በጠበቀ ሁኔታ የቤት ውስጥ መስተንግዶ ግልጋሎቶችን መስጠት ይችላሉ
- ቡና ቤቶች፣ ክለብና መዝናኛዎች የርቀት መጠንን ጠብቆ ከ150 ያልበለጡ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ደንበኞችን ቤት ውስጥ 500 ውጪ ማስተናገድ ይችላሉ
- የፀጉርና የውበት ሳሎን የርቀት መጠንን ጠብቆ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ደንበኞችን ማስተናገድ ይችላሉ
- የማኅበረሰብ ስፖርቶች ይቀጥላሉ
ሙዋዕለ ሕፃናት
- ሁለቱም ወላጆቻቸው ክትባት የተከተቡ ሕፃናት ከኦክቶበር 26 ጀምሮ ሙዋዕለ ሕፃናት መገኘት ይችላሉ
ትምህርት ቤቶች
- ከኦክቶበር 5 አንስቶ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሳምንት አምስት ቀን መማሪያ ክፍሎች ውስጥ ሆነው መማር ይጀምራሉ
- ከአንደኛ ክፍል በታች ያሉ ተማሪዎች በሳምንት ሶስት ቀናት በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ተገኝተው ይማራሉ
- ከ 1ኛ እስከ 2ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ከኦክቶበር 18 አንስቶ በሳምንት ለሁለት ቀናት መማሪያ ክፍሎች ውስጥ ተገኝተው ይማራሉ
- የተቀሩት ተማሪዎች ከኦክቶበር 26 ጀምሮ በሳምንት ከሁለት እስከ አምስት ቀናት መማሪያ ክፍሎች ውስጥ ሆነው ትምህርታቸውን ይከታተላሉ ሥራ
- ሙሉ ክትባት የተከተቡ የቢሮ ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ ይችላሉ
- የኮንስትራክሽን ሠራተኞች 70 ፐርሰንት ሙሉ ክትባት ደረጃ ላይ ሲደርሱ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች በሙሉ አቅማቸው ተጋሮቻቸውን ማከናወን ይፈቀድላቸዋል
ልዩ ሥነ ሥርዓቶች
- ሙሉ ክትባት የተከተቡ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች የክትባት ደረጃ 80 ፐርሰንት ሲደርስ የሠርግ፣ የቀብርና ሃይማኖታዊ ግልጋሎት ሰጪዎች ከ450 ላልበለጡ ቤት ውስጥ ከ500 ላልበለጡ ታዳሚዎች ከቤት ውጭ ግልጋሎቶቻቸውን መስጠት ይችላሉ