- የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከዳር እስከ ዳር የሚጣሉ ድፍን እገዳዎች የኦሚክሮንን መስፋፋት ከመግታት ይልቅ ከቶውንም በሰዎች 'ሕይወት ላይ ጫናን እንደሚያሳድር' አሳሰቡ። ቫይረሱ በአሁኑ ወቅት 23 አገራት ውስጥ ተሰራጭቶ ይገኛል።
- ድርጅቱ ለተላላፊ በሽታ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ሰዎች ጉዟቸውን ቢገቱ የተሻለ እንደሚሆን አመላካች መምሪያ አውጥቷል።
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ሰባተኛ ሰው በኦሚክሮን መጠቃቱ ተገለጠ። ግለሰቡ ደቡብ አፍሪካ እንዳልነበረም ተነግሯል።
- የቪክቶሪያ ጤና ሚኒስትር ኦሚክሮን ማኅበረሰቡ ውስጥ ሳይዘልቅ እንዳልቀረ ጠቆሙ። እስካሁን ድረስ ቪክቶሪያ ውስጥ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልተመዘገበም።
- የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁትር ከፍተኛ በመሆኑ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እምብዛም እንደማያሳስብ ተናገሩ።
- የኩዊንስላንድ ፕሪሚየር አንስታዥያ ፓለሼይ ትናንት ጎልድ ኮስት ውስጥ በኮሮናቫይረስ መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ በጥቁር ዓርብ ዕለት በርካታ ቦታዎች መዘዋወሩን ገለጡ።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,419 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 10 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 271 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ስምንት፣ ኖርዘርን ቴሪቶሪ አንድ ሰው በቫይረስ የተጠቃባቸው መሆኑን መዝገበዋል።
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤