የተለያየ በህል ያላቸው አውስትራሊያውያን ከአሁን በኋላ በቋንቋቸው የሚናገሩ የአእምሮ ጤና ባለሙያዎችን ማግኘት ይችላሉ

Some of the professionals listed on HeartChat.

Some of the professionals listed on HeartChat. Source: HeartChat.com.au

የተለያየ በህል ያላቸው አውስትራሊያውያን ከአሁን በኋላ በቋንቋቸው የሚናገሩ የአእምሮ ጤና ባለሙያዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ሲሞናቲ ለመጀመሪያ የአእምሮ ጤና ባለሙያን ያየቸው ገና ታዳጊ ወጣት ሳለች በትምህርት ቤት ነበር ፡፡

የሜልበርን ነዋሪ የሆነችው ይህች ሴት አሁን በ20ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ትገኛለች፡፡በዚያን ወቅት በትምህርት ጫና እና ከእርሷ ይጠበቅ በነበርው ውጤት ምክንያት ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነበረች፡፡

“ በዚያን ወቅት የብቸኝነት ስሜት ይሰማኝ ነበር፤ እንዲሁም በአውስትራሊያ እና በአደግኩበት በባንግላዲሽ ሂንዱ ባህሎች መካከል ያሉትን ግጭቶች በተመለከተ ለይቶ ለማወቅ በማደርገው ሂደት ውስጥ  ከፍተኛ የአእምሮ ግጭት ውስጥ ነበርኩ ” ስትል ለኤስ ቢ ኤስ ዜና ክፍል ተናግራለች ፡፡

ቆይታም ከእርሷ ባህል ጋር የተለየ የስነ ልቡና ባለሙያን ለማየትችላ ነበር ሄደች፡፡ ይሁንና ከልምዷየተማረቸው የእርሷን ባህል እና ሁኔታ ሊረዱላት ያለመቻላቸውን ነው፡፡

“ ምናልባትም በመሃከላችን ያለው የባህላችን ልዩነት ነው ” ስትል ተናግራለች  

“ መልካም ሊሆን ይችል የነበረው አመጣጡ ከደቡብ እስያ አካባቢ እና ፤ ሂንዱ ቢሆን ኖሮ በወቅቱ የነበረብኝን ተግዳሮቶች ለመለየት ይረዳኝ ነበር፡፡”

ባለፈው ቅዳሜ ይፋ የተደረገው እና  በድረ ገጽ የሚገኘው መረጃ አላማውም ይህ ነው፡፡ ህርት ቻት ( HeartChat) በመባል የሚታውቅ ሲሆን አግልግሎቱም  በአውስትራሊያ የሚኖሩትን እና ከተለያየ ባህል እና ቋንቋ የመጡ ሰዎችን እነሱን ከሚመስሏው የአእምሮ ጤና ባለሙያዎችን ጋር ማገናኘት ነው ፡፡

ይህ ልዩ አገልግሎት ሁሉንም የመስኩን ባለሙያዎች በአንድ ላይ ለማግኘት የሚያስችል ሲሆን ፤ የተገልጋዩን ቋንቋ የሚናገሩ የምክር አገልግሎት እና ሳይካትሪስቶችን ፤ ወይም  የጋራ ባህል እና እምነት ያላቸውን ባለሙያዎች በቀጠሯቸው ሰአት ወይም ክፍያን ሲፈጽሙ በማቅረብ ፤ አልያም ደንበኞቹ ምርጫቸው የስልክ አገልግሎት ከሆነ ( telehealth) ቀጠሮን ለመያዝ እርዳታ መስጠትን ያጠቃልላል፡፡

ዶ/ር ጁዲ ታንግ የአእምሮ የስነልቡና ባለሙያ ሲሆኑ የዚህ ልዩ አገልግሎት ሃሳብ አመንጪ እንዲሁም በገንዘብ የሚደጉመው ተቋም ቪክቶሪያ መድብለባህል ኮሚሽነር  ናቸው ፡፡

ይህ ልዩ አገልግሎት በዚህ ሙያ ከሰራ እና ከእስያ ባህል ከመጡት ከእሳቸው የስራ ልምድ የተገኘ ውጤት ነው ፡፡

“ ቀድሞ የነበር ደንበኛዬ ያለኝ ይህንን ነበር ፡ ‘ቋንቋዬን የሚናገር እና ባህሌን የሚያውቅ  እንዳንቺ ያለ ሰውን ማግኘት ለእኔ በጣም ከባድ ነበር ፤  ይህንን ቀጠሮ ለመያዝ ረጅም ጊዜ ፈጅቶብኛል’ ሲሉ የማንደሪን ቋንቋ ተናጋሪዋ ዶ/ር ታንግ ተናግረዋል ፡፡”

“ እኔ የምሻው የአእምሮ ጤና አገልግሎት እርዳታ ለማህበረሰባችን እንደልብ የሚገኝ ማድረግ  ነው፡፡”

ባህልን የሚመጥን እርዳታ

አንዳንድ ጊዜ በሀይማኖትዎ መነገር የሌለባቸውን ፤ የባህል ልዩነትን ፤ የፖለቲካ እና  የጾታ ምርጫዎትን በተመለከተ ማስረዳት ሳይገባዎ ሊረዳዎት የሚችንል ሰው ማግኘት የሚሰጠው እረፍት ከፍተኛ እና ክዚያም አለፍ ሲል ህይወትን ታዳጊ ነው፡፡

ዶ/ር ታንግ ያካፈሉት አንድ የስነ አእምሮ ባለሙያ ከእስያ መጥ የሆኑ ደንበኛቸውን ለማበረታታት እና በህይወታቸው አወንታው ለውጥ እንዲያመጡ የመከሯቸውን አስመልከተው ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡ ባለሙያውም ያሉት

 “ ይህንን ለእርስዎ ለራስዎ ሲሉ ያድርጉት ይችላሉ ” የሚል ነበር ፡፡  ይሁንና ግለሰቡ የመለሱት “ እኔ ከእስያ የመጣሁ እንደመሆኔ መጠን ለቤተሰብዎ ሲሉ ያደርጉት ይችላሉ ቢሉኝ ኖሮ የተሻለ ውጤት ሊኖረው ይችል ነበር ” በማለት እንደነገሩ ዶ/ር ታንግ ተናግረዋል

አያይዘውም ባህልን ካለመረዳት የተነሳ የሚሰነዘሩ በርካታ እና አላዋቂ የሚያስብሉ የባለሙያ አስተያየቶችም እንዳሉ አንስተዋል፡፡

“ የነባር ህዝቦች አባል የሆነ አንድ ሰው  ‘ ወደ ጫካ ተመለስ እና ከህዝብህ ጋር ተቀላቀል’ ተብሏል ፡፡እንዲህ ያለው  ሁኔታ ሁሉም የነባር ህዝቦች ተለይተው የሚታወቁበት አይደለም ፡፡” ሲሉ ተናግረዎች

“ እንዳለመታደል ሆኖ አንዳንድ ጊዜ የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች ከራሳቸው ተነስተው የሚሰጡዋቸው ግምታዊ ብያኔዎች ከባህል እና እምነት አኳያ ሲታዩ ትክክለኛ ላይሆኑ ይችላሉ ፡፡”

ዶ/ር ታንግ እንደሚሉት ብዙውን ጊዜ ከባህል እና ከቋንቋ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሰዎች  እርዳታን እንዳይሹ ከሚያግዷቸው ነገሮች መካከል ዋነኛዎቹ ናቸው ፡፡

“ አንዳንድ ጊዜ ነገሮችን ባልሆነ መንገድ ሲረዱት ፤ ያኔ ነው ግለሰቡ ፍላጎቱን የሚያጣው እና የአእምሮእ ጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን እርዳታ ከመሻት የሚታቀበው፡፡  ይሁንና በግልጽ መናገር የምንፈልገው መድብለ ባህል የሆኑት የማህበረሰባችን አካላት አሉታዊ የሆነ ልምድን እንዲያዳብሩ በፍጹም አንፈልግም  ፡፡”

ከየት እንደመጡ አውቃለሁ ‘

ከተለያዩ ባህል እና ቋንቋዎች የመጡ አውስትራሊያውያን የድጋፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለማግኘት ረጅም ጊዜ የፈጀ ችግሮን ይጋፈጣሉ፡፡ ምናልባትም በቋንቋቸው ወይም በባህላቸው እንዲሁም ባለባቸው የአእምሮ ጤና ችግር ምክንያት ከማህበረሰባቸውም ጭምር መገለልን ያስተናግዳሉ ፡፡ እንዲሁም እንክብካቤን እና እርዳታን  ለማግኘት ጉዞዋቸውን ከየት መጀመር እንዳለባቸው ለማወቅ በሚጥሩበት ሰአት ሌሎች ችግሮችን ይጋፈጣሉ ፡፡

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በአእምሮ ተቋማት ዙሪያ የስልክ ጥሪዎች የናሩበት እና ባለሙያዎችን ለማየት የሚያስጠበቀው ጊዜ ከመቼውም ጊዜ በለይ ከፍ ያለበት እንዲሁም ሰዎች እርዳታን ለማግኘት ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ የሻቱበት ወቅት ነበር፡፡

“ በሁሉም ላይ አውንታዊ ተጽእኖ ያደረገ ቢሆንም በተለይ የመድብለ ባህል የማህበረሰብ አባለት በሆኑት እና ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት ገደብ ባለባቸው ላይ ከፍተኛ ነው ፤ይህ ደግሞ ለአብዛኞች ከባህል አንጻር ህይወታቸው ለይ ከፈተኛ ተግዳሮትን ጥሏል ሲሉ ዶ/ር  ታንግ ተናግረዋል ፡፡”

ሌላኛዋ የስነ ልቡና ባልሙያ እና ሲድኒ መሰረቱን ያደረገውን ሄልዝ ቻት (HealthChat) የተቀላቀሉት ዶ/ር ጀሊና ዜልስኮቭ ዶሪች እንዲሁ መሰረታቸው ከሰርቢያ ነው፡፡

ዶ/ር ዶሪች አምስት የባልካን ቋንቋዎችን እና የቡልጋሪያ ቋንቋን መናገር የሚችሉ ሲሆን ፤ እንደሳቸው ልምድ ከሆነ፤ አንዳንድ ደንበኞች ስልክ የሚደውሉት ቋንቋቸውን የሚናገር ባለሙያን ለማግኘት ነው፡፡

“ አንዳንዶቹ ምንም አይነት የእንግሊዝኛ ቋንቋን አይችሉም ፤ ራሳቸውን በፍጹም መግለጽ አይችሉም ብለዋል፡፡” ዶ/ር ዶሪች   

በተለይ ከስነ አእምሮ አንጻር ለምሳሌ ስለራስ ፍላጎት ፤ ግንኙነት እና ስሜት መናገር በሚፈለጉብት ጊዜ በእርግጥም እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡”

ዶ/ር ዶሪች እንደሚሉት ከሆነ ደንበኞቻቸውን ስለ ባህላቸውና ልምዶቻቸው ፤ ወጎቻቸው ወይም በልዩነታቸው ሳቢይ ሊኖር ስለሚችም የመገለል ስሜት ሳይሰማቸው በቀላሉ ሊረዷቸው እንደሚችሉ ገልጸዋል ፡፡

“ ለእኔ እነሱን መረዳት በጣም ቀላል ነው፤ ለምን ቢሉ ከየት እንደመጡ ስለማውቅ ” ብለዋል

“ ስለተለያዩ በህሎች ማንበብ ይችሉ ይሆናል፡፡ ይሁን እና ከዚያ ባህል ውስጥ ካልወጡ በቀር በምንም አይነት ሰዎቹ ያለፉበትን ሁኔታ ለመረዳት አይችሉም፡፡”

ዶ/ር ዶሪች ከእስያ የመጡ ድንበኞችን የሚረዱ ሲሆን ደንበኞቻቸውም እንደ እነሱ መጤ የሆነ ባለሙያን ማየት እንደሚመርጡ መናገራቸውን አክለዋል፡፡

“ እኔን ይቀርቡኛል ፤ የባህል ማንነት ጉዳዮችን በተመለከት ከእኔ ጋር መነጋገርን ይሻሉ ፡፡  የሚቀርቡኝም እኔ ከሌላ ባህል እንደመጣሁ ስለሚያውቁ ነው ፤ እኔ የምኖረው እዚህ ነው የኖርኩት ግን እዚያ ነው ፤ በእኔ ውስጥ ብዝሀነት አለ፡፡ ” 

የአእምሮ ጤና ባለሙያዎችን ሙሉ ዝርዝር በተመለከት ወይም ለአገልግሎቱ መመዝገብ የሚሹ ከሆነ ይጎብኙ፡፡   

በተጨማሪም በቋንቋዎ የአእምሮእ ጤናን በተመለከተ በአውስትራሊያ እርዳታን ማግኘት ካሻዎ ከኤስ ቢ ኤ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

አንባቢዎች የአደጋ ጊዜ ድጋፍን የሚሹ ከሆነ ላይፍ ላይን የሚባለውን በስልክ ቁጥር 13 11 14 ፤ ህይወትን ከማጥፋት የሚታደግ እርዳታን ለማግኘት በ 1300 659 647 እንዲሁም ልጆችን በተመለከተ እርዳታን ላማግኘት 1800 55 1800 (እድሜያቸው ከ 5 እስክ 25 ላሉት ) ተጨማሪ መረጃዎች ከ እና ይገኛል ፡፡

ከተለያዩ ቋንቋዎች እና ባህል ለመጡ እርዳታን ይሰጣል ፡፡


Share
Published 11 October 2020 8:27pm
Updated 11 October 2020 8:33pm
By Julia Carr-Catzel
Presented by Martha Tsegaw
Source: SBS News


Share this with family and friends