የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የዓለም አቀፍ ድንብሮቹን የመክፈቻ ጊዜ ከዲሴምበር 1 ወደ ዲሴምበር 15 አሸጋገረ።
የጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት ለዓለም አቀፍ ድንበሮቹ መከፈቻ ጊዜ ለ14 ቀናት እንዲገታ የተደረገው በኦሚክሮን ኮቪድ-19 ሳቢያ እንደሆነ አመላክተዋል።
ቀደም ብሎ በተያዘው ዕቅድ መሠረት 200,000 ሠራተኞችና ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ወደ አውስትራሊያ ከረቡዕ ዲሴምበር 1 ጀምሮ መዝለቅ ይጀምሩ ነበር።
የጉዞ ገደቡ ከጃፓንና ደቡብ ኮሪያ የሚመጡ ሙሉ ክትባት የተከተቡ መንገደBኦችንም ይመለከታል።