የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ኅዳር 7 ቀን 2015 በማር ኧ ላጎ መኖሪያቸው ለ2024ቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ውድድር በዕጩነት እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል።
አቶ ትራምፕ በወቅቱ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ድል ተነስተው ዋይት ሐውስን ከመልቀቃቸው በፊት ከጃኑዋሪ 20, 2017 / ጥር 12, 2013 እስከ ጃኑዋሪ 20, 2021 / ጥር 12, 2013 የዩናይትድ ስቴትስ 45ኛው ፕሬዚደንት ሆነው ስልጣን ላይ ቆይተዋል።