ጤናና ደኅንነትዎን ለመታደግ አሁኑኑ ሊከውኗቸው የሚችሉ አምስት ነገሮች

ጤናና ደኅንነትዎን ከመጠበቅ ጋር ተያያዥ የሆኑ ትሩፋቶች አሉ። ያን ባለማድረግም በአብዛኛው አካላዊና አዕምሯዊ ተፅዕኖ ሊያድርብዎት ይችላል።

Mind Your Health.jpg

Mind Your Health. Credit: iStockphoto / DisobeyArt/Getty Images/iStockphoto

የአካላዊ እንቅስቃሴና ጤና ፕሮፌሰር አን ታይደማን፤ ሁለት ነገሮችን በየዕለቱ በመከወን ጤናን በጥሩ ሁኔታ ጠብቆ ለማቆየት እንደሚቻል ይናገራሉ። እኒያም አካላዊ እንቅስቃሴና የአመጋገብ ሚዛን ናቸው።

ሌሎቹ የአልኮል መጎንጨት መጠን ላይ ገደብ ማበጀት፣ ከማጨስ መቆጠብና ማኅበራዊ ግንኙነትን የሚያካትቱ ናቸው።

1. አካላዊ እንቅስቃሴ

ፕሮፌሰር ታይደማን አካላዊ እንቅስቃሴን ማዘውተር አካላዊ፣ አዕምሯዊና ማኅበራዊ ጤናን ብቻ የሚያጎለብት ሳይሆን በእርጅና ዕድሜ የሚከሰቱ ሕመሞችን ከወዲሁ ለመከላከል እንደሚያግዝ በርካታ ማስረጃዎች የሚያመለክቱ መሆኑን ይገልጣሉ።

አንድ ግለሰብ ዛሬ ወይም በዚህ ሳምንት ውስጥ የሚከውነው የወደፊት ትሩፋት እንዳሉት የሲድኒ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሯ ይናገራሉ።

ፕሮፌሰር ታይደማን አንድ ሰው ምን ያህል የአካላዊ እንቅስቃሴ ተሳትፎ ሊያደርግ እንደሚገባ ሲገልጡ፤ የእንቅስቃሴው መጠን በግለሰቡ ዕድሜ፣ ስር በሰደደ ሕመም መያዝና የግብረ አካል ጉዳተኝነት ሁኔታ እንደሚወሰን በመጥቀስ ለመመሪያነት እንዲበጅም ወደ ዓለም ጤና ድርጅት መምሪያዎች አመላክተዋል።

አክለውም “በየትኛውም ዕድሜ ወይም የግብረ አካል ጉዳተኛ ደረጃ እንገኝ አካላዊ እንቅስቃሴ ለሁሉም ሰው ማለፊያ ነው።

“በመምሪያዎቹ መሠረት የአካላዊ እንቅስቃሴ መጠንን መከወን ባይችሉ እንኳ ፤ የተወሰነ አካላዊ እንቅስቃሴ መጠን አሁን ከሚያደርጉት በትንሹ ሻል ያለ የጤና ትሩፋቶችን እንደሚያስገኝልዎ የምርምር ግኝቶች በግልፅ ሁኔታ ያመልክታሉ" ብለዋል።

ፕሮፌሰሯ አካላዊ እንቅስቃሴ በተለያዩ መልኮች እንደሚከወንና የግድ መዋቅራዊ በሆነ ስፖርት ወይም የእንቅስቃሴ ቡድን መወሰን እንደሌለበትም ልብ ሲያሰኙ፤

“በትርፍ ጊዜዎ የሚያደርጉት የእግር ጉዞ፣ የቤት ውስጥ ሥራዎች፣ በቤት ዙሪያ የሚከወኑ እንቅስቃሴዎች፣ የጓሮ እርሻ ኩትኮታዎች ይሁኑ፤ ሁሉም ለጤና ማሻሻያ አስተዋፅዖ አላቸው” ብለዋል።

2. የተመጣጠነ አመጋገብ

ፕሮፌሰር ታይደማን፤ የተመጣጠነ ምግብን መመገብ የረጅም ጊዜ ሕመም ተጋላጫነትንና አለቅጥ ውፍረትን ለመቀነስ ጠቃሚ ስለመሆኑም ያስረዳሉ።

ጥሩ የተመጣጠነ ምግብ ሰውነትዎን በጥሩ ሁኔታ ለማንቀሳቀስ መልካም ነው። አጥንትዎን ያጠነክራል፤ ኃይልም ይሰጥዎታል።

“እነዚህ ሁሉ በጣም ጠቃሚ ናቸው። በጣሙን ከበሰለ ምግብና በርካታ ስኳር ይልቅ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ሕብረተሰቡ ውስጥ ተከስቶ ያለ ትልቅ ጉዳይ ነው” ሲሉም አክለዋል።


ስለ ምግብ ዓይነቶች፣ መጠን፣ የምግብ ፈርጆችና የአመጋገብ ዘዬዎች መረጃን ይሰጣል።

አውስትራሊያውያን ራሳቸውን ስብን ካከማቹ፣ ጨው ከበዛባቸው ምግቦችና አልኮል ተቆጥበው ከአምስት የምግብ ዘርፎች መጠነ ሰፊ ተመጣጣኝ ምግቦችን በመመገብ እንዲረኩ ያበረታታል።

3. የአልኮል መጠንዎን ይገድቡ፤ ከማጨስ ይገቱ

ፕሮፌሰር ታይድማን አልኮልን መገደብና ሲጋራን ከማጤስ መታቀብን አስመልክተው ሲናገሩ፤ “እኒህ የአኗኗር ዘይቤዎች ለበርካታ ሕመሞች የተጋላጭነት አስባቦች ስለ መሆናቸው እናውቃለን” ብለዋል።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ገለጣ፤ አልኮልን በመጎንጨት ሳቢያ በዓመት በመላው ዓለም 3 ሚሊየን ያህል ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩም ለግብረ አካል ጉዳቶችና ለጤና መጓደሎች ይዳረጋሉ።

የአውስትራሊያ የጤናና ደኅንነት ተቋም ዳታ እንደሚያመልክተውም በ2020 ከአልኮል ጋር በተያያዘ 1,452 ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡና አብዛኛዎቹም (73 ፐርሰንቱ) ወንዶች መሆናቸውን አመልክቷል።

በ2020 የተከለሱት የአውስትራሊያ አልኮል መምሪያዎች የጤና አደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የአልኮል ጉንጨታ መጠን ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

በተጨማሪም፤ የካንሰር ምክር ቤት ከአልኮል ነፃ ቀናትንና ጥማትን በውኃ ማርካትን አካትቶ ከአልኮል ልማዶች ለመላቀቅ 12 ጥቆማዎችን በምክረ ሃሳብነት አቅርቧል

በተጨማሪም ኔታዎችን ከማብዛቱና ለሞት ከመዳረጉም በላይ፤ቀንሳል።

4. የማኅበራዊ ግንኙነትን መቀጠል

ፕሮፌሰር ታይደማን በሕብረተሰቡ ውስጥ ብቸኝነት "ትልቅ ችግር" እንደሆነና ሌላው ቀርቶ አንድ ግለሰብ በሰዎች ተከብቦ እያለ እንኳ በአብዛኛው "የግንኙነት መላላት" እንዳለ ሲናገሩ፤

“በዙሪያዎ ካሉ ሰዎችና ከምንኖርበት ሕብረተሰብ ጋር የመገናኘት ስሜት በውስጣችን መኖር ነው።

“እርስዎ ለሌሎች ፋይዳ ያለዎት ሆኖ ከመሰማት ስሜት ጋር የተያያዘ ነው። እንዲሁም፤ እርስዎ ለሌሎች ያለዎትን ተከባካቢነት የሚያሳይ ነው። ሰብዓዊ ግንኙነት በጣሙን ጠቃሚ ነው” ብለዋል።

በማከልም ስለ የግንኙነት መንገዶች ዘርፈ ብዙ ስለመሆናቸው በማንሳት በጎ ፈቃደኝነትንና ማኅበረሰቡ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ መሆንን ሲያመላክቱ፤

“[በጎ ፈቃደኝነት] እንደ አንድ ቡድን አካል የጋራ ዓላማን ከመጋራት አኳያ አንዱ ከሌሎች ሰዎች ጋር ማኅበራዊ ግንኙነትን የማዳበሪያ መንገድ ሊሆን ይችላል፤ ለዚህም ስፖርት አንዱ ጥሩ መንገድ ነው።

“አንድ ቡድን አቀፍ ስፖርት ይኖርዎታል፤ ሁላችሁም በዚያ መንገድ በመተሳሰር የምታልሙት ተመሳሳይ ውጤትን ነው” ብለዋል።

ይሁንና የተወሰኑ ሰዎች ብቻቸውን በማሳለፍ ደስታን እንደሚያገኙ ሲያመላክቱም፤

“ምንም እንኳ [እኒህ ግለሰቦች] ብቻቸውን ቢሆኑም በሌላ መንገድ ተመሳሳይ የሆነ ግንኙነት አላቸው” ሲሉ ተናግረዋል።


ቢዮንድ ብሉ ማኅበራዊ ግንኙነትን ጠብቆ ስለመቆያ መስፈርቶች ምክረ ሃሳቦች አሉት
እንደ ስካይፕ፣ ዙም፣ ፌስታይምና የቤት ውስጥ ፓርቲን የመሳሰሉ የቴክኖሎጂ ውጤት ኧፖችን በመጠቀምም የቡድን ቪዲዮ ግንኙነት ማድረግም እንደ አንድ ማኅበራዊ መገናኛ ያገለግላል።

ድርጅቱ በታካይነትም፤ እንደ መጽሐፍ ክለብ፣ የጨዋታ ምሽት፣ የቤተሰብ እራት፣ የዳንስ ፓርቲዎች ወይም ከወዳጅዎ ጋር መደበኛ ማኅበራዊ ግንኙነትን በቀጠሮ ማከናወንን በምክረ ሃሳብነት ይቸራል።

5. ራስዎንና የሚያስቡላቸውን ሰዎች ደኅንነት ያረጋግጡ

ፕሮፌሰር ታይደማን ራስዎንና የሚያስቡላቸውን ሰዎች ደኅነንት ማረጋገጥን አስመልክቶ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ገደብ የተጣለበት ወቅት አንዱ ማለፊያ ምሳሌ እንደሁ ሲያነሱ፤

“ያ በጣሙን ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ። ለምሳሌ ያህል በገደቡ ውስጥ ስልለ ነበሩቱ የራሴ አረጋውያን ወላጆች የሚያስፈልጋቸው ነገሮች ይኖሯቸውን እንደሁ በማሰብ መጨነቄን አውቃለሁ።

“ሆኖም በአብዛኛው በጣሙን የበዛ ጭንቀትና መታወክን ተሸክመው ያሉ መሆንዎ አይታወቅዎትም። ስለ ራስዎ ደኅንነት ያስቡ። እንደ እውነቱ ከሆነ የሚያደርጓቸው ነገሮች ለእርስዎ ደኅንነት መልካም ስለመሆናቸው ማረጋገጡ በጣሙን ጠቃሚ ነው” ብለዋል።

የብላክ ዶግ ኢንስቲትዩት አንድ ግለሰቦች በየሳምንቱ ስሜቶቻቸውን፣ አካሎቻቸውን፣ ዕንቅልፋቸውና ዕሳቤዎቻቸውን አካትተው የአዕምሮ ጤናቸውን እንዲያረጋጡ ምክረ ሃሳቦቹን ይቸራል።

እርዳታን የሚሹ አንባቢያን ለ24-7 የቀውስ እገዛ ወደ ላይፍላይን በ 13 11 14, ሕይወትን የማጥፋት ሙከራ የስልክ ጥሪ ምላሽ አገልግሎት በ 1300 659 467 እና ወደ የልጆች የእርዳታ መስመር በ 1800 55 1800 (ዕድሜያቸው ከ 5 እስከ 25 ለሆኑ)። ለተጨማሪ መረጃ የ እና  ድረ ገጾችን ይጎብኙ።

ባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅነት ላላቸው ሰዎች እገዛ ያደርጋል።





Share

Published

By Kassahun Seboqa Negewo, SBS-ALC content
Source: SBS

Share this with family and friends