ሙሉ የኮሮናቫይረስ ክትባት የተከተቡ አውስትራሊያውያን ለልዩ ይለፍ ፈቃድ ሳያመልክቱ ወደ ውጭ አገር መሔድና መመለስ እንዲችሉ ተፈቀደ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ከኖቬምቨር 1 ጀምሮ የልዩ ፈቃድ ጥየቃ እንደሚያበቃ አረጋግጠዋል።
ይህንኑ አስመልክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን አውስትራሊያ በፈንታዋ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሲናፖራውያን ወደ አውስትራሊያ እንዲመጡ ለመፍቀድ መቃረቧንና ከአንድ ሚሊየን ተኩል በላይ አውስትራሊያውያን ዓለም አቀፍ የክትባት ምስክር ወረቀትን ተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው ላይ የጫኑ መሆኑን ተናግረዋል።
የጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንትም በበኩላቸው፤ አውስትራሊያውያን ወደ ባሕር ማዶ ሲጓዙ ዕውቅና ያለው ሁለት ዙር ክትባት መከተባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ሊይዙ እንደሚገባና የሁለተኛ ዙር ክትባታቸውን ሊከተቡ የሚገባውም ቢያንስ ወደ ውጭ አገር ለመሔድ ከመነሳታቸው አንድ ሳምንት በፊት መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።