አንኳሮች
- የአውስትራሊያ የቤተሰብ ጥናቶች ኢንስቲትዩት አውስትራሊያ ውስጥ 14 ፐርሰንት አረጋውያን በተደጋጋሚ በሰዎች ሆን ተብሎ የመጎሳቆል ተሞክሮዎች አንደገጠማቸው ግምት አለው
- ጁን 15-2020 ሉላዊ የጉስቁል አረጋውያን ግንዛቤ ቀን ታስቦ ይውላል
- ባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅነት ላላቸው ማኅበረሰባት በሁሉም ስቴትና ግዛቶች በየቋንቋቸው እርዳታዎችን ማግኘት ይችላሉ
እንደ አውስትራሊያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አባባል፤ የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ከሚያደርሰው ፈጣን የጤና ጉዳት ባሻገር አውስትራሊያ ውስጥ ባሉ አረጋዉያን ላይ ይበልጥ ተጋላጭነትንና የአደጋ ስጋቶችን አሳድሯል።
የቀድሞዋ የአውስትራሊያ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልና የጸረ ዕድሜ መድልዖ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ኬይ ፓተርሰን፤ ማኅበራዊ መገለል ማኅበራዊ በይነ መረቦችንና የጤና ግልጋሎትች ላይ ስጋቶችን ስለሚያሳድር ለአረጋውያን ለጉስቁልና ለመዳረግ አንዱ ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ገልጠዋል።
የተወሰኑ አረጋውያን ከቤት ያለመውጣት ገደቦች ሳቢያ ከጉስቁልና አድራሽ ጋር አንድ ላይ በመዋላቸው ወይም ቀደም ሲል እርዳታን ያገኙባቸው ወደነበሩ ሥፍራዎች መሔድ ባለመቻላቸው ለአደጋ ተጋላጭነታቸው ከፍ ብሏል።

Source: Getty Images/ KLH49
አረጋውያንን ማጎሳቆል በማኅበረሰባችን ውስጥ ሥፍራ የሌለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ነው።
የዓለም ጤና ድርጅት የአንዴ ወይም ተደጋጋሚ የማጎሳቆል ድርጊት፣ አግባብ ያለው ድርጊትን አለመፈጸም፣ በማናቸውም ዓይነት ግንኙነት ወቅት እምነትን በማጓደል በአንድ አረጋዊ/ት ላይ የሚደርስ ጉዳት ወይም ጭንቀትን በአረጋውያን ጉስቁልና ተግባርነት ይፈርጃል።
ዶ/ር ፓተርሰን ማኅበራዊ አካታችነትንና በአካላዊ ርቀት ወቅትም አብሮነትን በመተግበር አውስትራሊያውያን በአረጋውያን ላይ የሚደርሱ የማጎሳቆል ድርጊቶችን ለመግታት እንደሚችሉ ያሳስባሉ።

Source: Getty Images/ delihayat
ከሕይወታችን ጋር የተቆራኙትንና አጎራባቾቻችን ከሆኑት ጋር መስተጋብሮቻችንን በመቀጠልና ደኅነታቸውን በማረጋገጥ ሁላችንም የየድርሻችን ሚና በመወጣት በአረጋውያን ላይ የሚደርሱ ጉስቁልናዎችን ማክሰም እንችላለን።
ዶ/ር ፓተርሰን አውስትራሊያውያን ሰኞ ጁን 15 - 2020 ሉላዊ የአረጋውያንን ጉስቁልና ቀንን አስበው እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል።
አያይዘውም፤ ጉስቁልና የደረሰባቸው አረጋውያን፣ ወይም በረጋውያኑ ላይ ሲደርስ የተመለከቱ ወደ ብሔራዊ የአረጋውያን ጉስቁልና የስልክ መስመር 1800 353 374 በመደወል እርዳታን እንዲያገኙ አበረታትተዋል።
ሁላችንም ጥረቶችን በማድረግ አረጋውያን በዚህ አዋኪ ወቅት ብቻቸውን እንዳልሆኑ ልናሳውቃቸው ይገባል።
የብሔራዊ አረጋውያን ጉስቁልና የእርዳታ መስመር እንደሚጠቁመው ከሆነ አረጋውያን የቤተሰብ አባል ወይም ተከባኪያቢያቸው ጉስቁልና እንደሚያደርሱባቸው ለማመን አይሹም። ከቶውንም ለጉስቁልና መዳረጋቸውንም ለመገንዘብ ይቸገራሉ።
በጥቅሉ፤ የሃፍረት ስሜቶች ሰለባዎችን ከሕዝብ ዕይታ እንደሚያገላቸው ተጠቁሟል።
አረጋውያኑ ለጉስቁልና መዳረጋቸውን ከሚያመላክቱ ምልክቶች ውስጥ ይህ ሆኗል ለማለት የሚያውኩ የአካል መጫር ወይም መጋጥ፣ የተሰበሩ የዓይን መነጽሮች፣ ከራሳቸው ጋር ማንሾካሾክ፣ መቀመጫቸው ላይ ሆነው አብዝተው መወዛወዝ፣ ከፍተኛ የክብደት መቀነስ፣ ንጽህና የጎደለው የአኗኗር ሁኔታዎች፣ ከመጠን በላይ ወይም ከልክ ያነሰ መድኃኒቶችን ስለ መውሰዳቸው መረጃዎች መገኘት፣ ድንገተኛ የፋይናንስ ለውጦችና የቁሳቁሶች ወይም ጥሬ ገንዘቦች ከአረጋውያኑ ቤት መጥፋት ዋነኛ ተጠቃሽ ናቸው።
በተለይም አረጋውያኑ ከባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ ማኅበረሰባት ውስጥ ከሆኑ፤ የእንግሊዝኛ ቋንቋ እጥረት ታክሎበት ለጉስቁልና መዳረጋቸውን ሪፖርት ለማድረግ ሌላ ተጨማሪ ተግዳሮት ይሆናል።

Source: Getty Images / Owaki/Kulla
እርዳታ ያለ መሆኑን ማወቁ በጣሙን ጠቃሚ ነው። ለአደጋ ተጋልጠው ያሉ ከሆነ ወዲያውኑ 000 ይደውሉ።
ነጻና ገመና አውጪ ያልሆነውን የብሔራዊ አረጋውያን ጉስቁልና የስልክ መስመርን በ 1800ELDERHelp, 1800 353 374 ማግኘት ይችላሉ።
በተጨማሪም ሁሉም ስቴቶች ግዛቶች ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ውጪ ተናጋሪ ለሆኑ አረጋውያን የድጋፍ ግልጋሎት ሰጪዎች አሏቸው።
In Victoria, you can get help by calling Senior Rights Victoria on 1300 368 821, or by visiting
In New South Wales, call Ageing and Disability Abuse Helpline on 1800 628 221, or visit
In Western Australia, call WA Elder Abuse Helpline on 1300 724 679, or visit
In Australian Capital Territory call the Older Persons ACT Legal Service (on (02) 6243 3436, or visit
In South Australia, call Aged Rights Advocacy Services on 1800 700 600, or visit
In Northern Territory, call the Elder Abuse Information Line on 1800 037 072, or visit