የሀይል አገልግሎቶች፤ የውሃና ግብር ክፍያን ለመፍጸም ለተችገሩ የወጣ ማሻሻያ
በገንዘብ ችግር ውስጥ ላሉ ቤተቦች እና አነስተኛ የንግድ ተቋማት የቀረበ አመቺ የአከፋፈል አማራጭ፡-
- በገንዘብ ችግር ውስጥ ያሉ ደንበኞች አገልግሎት በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ እንዳይቋረጥ
- እዳቸውን ለመክፈል እንዲችሉ በቂ ጊዜን በመስጠት ስማቸው እዳን በማይከፍሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ እንዳይገቡ መከላከል
- በወቅቱ ባለመከፈል ሳቢያ የሚጨመሩ እዳዎችን እና ወለድን ማንሳት
- አስፈላጊ የሚባሉ ሰራዎች በሚከናወኑበት ወቅት የታቀዱ የአገልግሎት መቋረጥ እንዳይኖሩ ማድረግ
- የአገልግሎ ክፍያዎቻቸውን (ቢሎቻቸውን ) መክፈል የሚችሉ ደንበኞች በተለመደው መልኩ መቀጠል ያለባቸው ሲሆን፤ ይህም ተቋማቱ በስራቸው ላይ እንዲቆዩ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡