እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ የቪክቶሪያን ከኮሮናቫይረስ ገደቦች መውጫ ፍኖተ ካርታ ዛሬ እሑድ ኦክቶበር 17 ይፋ አድርገዋል።
ፍኖተ ካርታውን ግብር ላይ ለማዋል እንደታሰበው ኦክቶበር 26 ሳይሆን ከሐሙስ እኩለ ለሊት ኦክቶበር 21 ጀምሮ እንዲያበቃ ከውሳኔ ላይ የተደረሰው ሙሉ ክትባት የተከተቡ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ቁጥር ሐሙስ ዕለት 70 ፐርሰንት እንደሚደርስ በመታመኑ ነው።
በዚህም መሠረት፤
ማኅበራዊ
- የሰዓት ዕላፊ አይኖርም
- ከቤትዎ ወጥተው ለመጓዝ የጉዞ ርቀት ገደብ የለም ሆኖም የሜልበርን ነዋሪዎች ፈቃድ ካላቸው በስተቀር ወደ ሪጂናል ቪክቶሪያ መጓዝ አይችሉም
- ቤትዎ ውስጥ ዕድሜያቸው ከ12 በላይ የሆኑ ክትባት የተከተቡ ከእነ ጥገኞቻቸው ከ10 ያልበለጡ ጎብኚዎችዎን ማስተናገድ ይቻላሉ
- እስከ 20 ሰዎች ከቤት ውጪ መሰባሰብ ይችላሉ፤ ክትባት የተከተቡ ቢሆን ይመከራል ሆኖም ግዴታ አልተጣለም
- የማኅበረሰብ ስፖርቶች አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ክፍት ይሆናሉ
የችርቻሮ ሱቆች
- የችርቻሮ ሱቆች ከቤት ውጭ አገልግሎቶችንና በቅድሚያ ትዕዛዝ ያዘዟቸውን መጥተው ለሚወስዱ ደንበኞች መስተንግዶዎቻቸውን መስጠት ይችላሉ
መስተንግዶዎች
- ቡና ቤቶች፣ ክለብና መዝናኛዎች የርቀት መጠንን ጠብቆ ከ 20 ያልበለጡ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ደንበኞችን በቤት ውስጥ ከ50 ያልበለጡ ውጪ ማስተናገድ ይችላሉ
- የፀጉርና የውበት ሳሎን የርቀት መጠንን ጠብቆ ከ5 ያልበለጡ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ደንበኞችን ማስተናገድ ይችላሉ
ትምህርት ቤቶች
- ከዓርብ ኦክቶበር 22 አንስቶ ተማሪዎች ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ይመለሳሉ።
ጋብቻና ቀብር
- እስከ 20 ሙሉ ክትባት በቤት ውስጥ ሠርግ ላይ 50 ከቤት ውጪ ባሉ የሠርግ ሥነ ሥርዓቶች ላይ መታደም ይችላሉ
- ቁጥራቸው ከ20 ያልበልጡ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ለቀስተኞች በቤት ውስጥ 50 ከቤት ውጪ ባሉ የቀብር ሥነ ሥር ዓቶች ላይ መገኘት ይችላሉ
ቤተ እምነቶች
- ቤት እምነቶች በእምነት ቤቶች ውስጥ ከ30 ላልበለጡ ከቤት ውጪ እስከ 100 ላሉ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ አማኒያን ሃይማኖታዊ ግልጋሎቶቻቸውን መስጠት ይችላሉ
ቪክቶሪያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓታት 1,838 ሰዎች ድ-19 ሲጠቁ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
እስካሁን ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች 88.05 ፐርሰንት የመጀመሪያ ዙር ክትባት 65.02 ፐርሰንት ሙሉ ክትባት ተከትበዋል።