በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ የመጀመሪያው ለኮቪድ - 19 ማርከሻ የሚሆን ክሊኒካዊ የክትባት ሙከራ ሜልበርን ውስጥ ተጀመረ

በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ የመጀመሪያው የሆነ በሰዎች ላይ የሚካሔድ የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ አውስትራሊያ ውስጥ ተጀምሯል።

Dr Nita Patel looks at a computer model showing the protein structure of a potential COVID-19 vaccine at Novavax labs in Maryland

Dr Nita Patel looks at a computer model showing the protein structure of a potential COVID-19 vaccine at Novavax labs in Maryland Source: Getty

ከሜልበርንና ብሪስበን የተውጣጡ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 59 የሚደርስ 130 ሰዎች ለክትባት ሙከራው ፈቃደኛ ሆነው ቀርበዋል።

በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም 10 ያህል የኮሮናቫይረስ ክትባቶች እየተሞከሩ ነው።

አውስትራሊያ ውስጥ በሜልበርን አልፍሬድ ሆስፒታል በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ የመጀመሪያው የሆነ ክሊኒካዊ ሙከራ ተጀምሯል።

ማርከሻ ይሆናል ተብሎ የታሰበው ክትባት የተዘጋጀው በዩናይትድ ስቴትሱ ኖቫቫክስ ኩባንያ ነው።

ኩባንያው ቀደም ሲል ለመርስ፣ ሳርስና ኢቦላ ክትባቶችን ፈብርኳል። 

 ኖቫቫክስ ክትባቱ ላይ መሥራት የጀመረው በወርኃ ጃኑዋሪ መገባደጃ ግድም ነው። 

ዶ/ር ግሪጎሪ ግሌን የኖቫቫክስ ምርምርና ልማት ፕሬዚደንት ክትባቱ የሚያተኩረው የሰውነትን የመከለከል አቅም በማዳበር ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርስ በማድረግ ቫይረሱን ማስወገድ እንደሆነ ገልጠዋል።

ዶ/ር ግሌን የክትባት ሙከራው ስኬታማ ከሆነ በዚህ ዓመት መጨረሻ መጠኑ 100 ሚሊየን የሚደርስ ክትባት ጥቅም ላይ ለመዋል ዝግጁ እንደሚሆን ተናግረዋል። 

 ስለ ኮሮናቫይረስ በቋንቋዎ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ካሹ sbs.com.au/coronavirus ድረ-ገጻችንን ይጎብኙ።

 

 

 

 

 


Share

Published

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends