5 ሚሊየን ያህል የሜልበርን ነዋሪዎች ከዛሬ ዕኩለ ለሊት ጀምሮ የደረጃ ሶስት የኮሮናቫይረስ ገደቦች ይጣልባቸዋል

ስለ ደረጃ ሶስት ገደቦች ሊያውቁ የሚገባዎት

Nearly 5 million Melbourne residents are going back into lockdown. Here’s what you need to know

Victoria Police will check motorists leaving the metropolitan Melbourne area. Source: AAP

ከ 4.9 ሚሊየን በላይ ሜልበርናውያን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በማገርሸቱ ሳቢያ ከጁላይ 8 ረቡዕ 11:59 pm ጀምሮ ለስድስት ሳምንታት ዳግም በሶስተኛ ደረጃ ገደቦች ስር ይሆናሉ። 

ቀደም ሲል ተጥለው ከነበሩት ገደቦችም መጠነኛ የሆኑ ለውጦች አሉ።

ገደቦቹ የተጣሉባቸው አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው?

ገደቦቹ የተጣሉት የሜልበርን ከተማንና ከከተማይቱ በስተሰሜን የሚገኘውን ሚችል ሻየርን አካትቶ በ31 ማዘጋጃ ቤቶች ዙሪያ ነው። 

እነሱም፤

Banyule, Hume, Moreland, Bayside, Kingston, Mornington Peninsula, Boroondara, Knox, Nillumbik, Brimbank, Manningham, Port Phillip, Cardinia, Maribyrnong, Stonnington, Casey, Maroondah, Whitehorse, Darebin, Melbourne, Whittlesea, Frankston, Melton, Wyndham, Glen Eira, Monash, Yarra, Greater Dandenong, Moonee Valley, Yarra Ranges እና Hobsons Bay ናቸው።

አዲሶቹ ደንቦች ምንድን ናቸው?

በደረጃ ሶስት ገደቦች ስር ሆነው ቤትዎን ለቅቀው ሊወጡ የሚችሉት ለአራት የተለያዩ ጉዳዮች ብቻ ይሆናል፤

  • አስፈላጊ ነገሮችን ከሱቅ ለመሸመት
  • ወደ ሥራና ትምህርት ቤት (ከቤት ሆነው መሥራት ወይም ትምህርትዎን መከታተል የማይቻልዎት ከሆነ)
  • ሕክምና ለማድረግ ወይም የሕክምና ክብካቤ ለማካሄድ
  • አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ
አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ እንደባለፈው ወቅት በገደቦች ስር ሆነው ወደ ገጠራማ ሥፍራዎች ለእግር ጉዞ መሄድ አይችሉም። እንቅስቃሴዎችዎ በከተማ ወሰኖች ውስጥ የተገደቡ ናቸው። 

ከሁለት ሰዎች በላይ መሰባሰብ አይቻልም።

ጎብኚዎችን ቤትዎ ውስጥ ማስተናገድ አይፈቀድም።

ካፌዎች፣ ምግብ ቤቶች፣ ክለቦችና መጠጥ ቤቶች ከቁም ሸምታና በትዕዛዝ ሸማቾች ካሉበት በማድረስ ግልጋሎቶች ብቻ የተወሰኑ ይሆናሉ።

የችርቻሮ ሱቆች የሸማቾችን መጠን በጠበቀ መልኩ ክፍት ይሆናሉ። 

ገበያዎች ለምግብና መጠጥ ሽያጭ ብቻ ይከፈታሉ።

የውበት ሳሎን፣ ግላዊ ግልጋሎቶች፣ የመዝናኛና ባሕላዊ ሥፍራዎች፣ የማኅበረሰብ ስፖርት ግልጋሎቶች ሲቋረጡ፤ የጸጉር ማስተካከያ ቤቶች ክፍት ሆነው ይቀጥላሉ።

የቀብር ሥነ ሥርዓት በ10 ለቀስተኞችና ሥነ ሥርዓቱን የሚያካሂዱ ሰዎች ታካይ ሆነው ይከናወናል።

ሠርግ በአምስት ሰዎች (ሁለት ሙሽሮች፣ ሁለት እማኞችና አንድ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት አስፈጻሚ) ውስን ሆኗል። 

ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በቀጥታ ሥርጭት ግልጋሎት ብቻ ይወሰናሉ። 

የሽርሽር ቤቶች ያላቸው ሰዎች ወደ እዚያ መዛወር ወይም መጓዝ አይችሉም።
Nearly 5 million Melbourne residents are going back into lockdown. Here’s what you need to know
Victorian Premier Daniel Andrews Source: SBS

ትምህርት ቤትን በተመለከተስ?

ሁሉም የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች መደበኛ የተርም ሶስት ትምህርታቸውን ሰኞ ዕለት ወደ  የትምህርት ቤቶቻቸው በመመለስ ያቀጥላሉ። ልዩ ትምህርት ቤቶችን አካትቶ፡፡

ከመዘጋጃ እስከ 10ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች፤ መንግሥት ከጤና ባለሙያዎች እነሱን አስመልክቶ ምክር እስከሚያገኝ ድረስ ለአንድ ሳምንት ተጨማሪ የዕረፍት ጊዜ ይኖራቸዋል።

የገደቦቹ አስፈጻሚ አካላት አሉ?

የአውስትራሊያ መከላከያና የፖሊስ ሠራዊት አባላት የገደብ ድንጋጌዎችን ያስፈጽማሉ።

ባለፈው ወር የቪክቶሪያ ፖሊስ የኮሮናቫይረስ ገደቦችን በጣሱ ግለሰቦች ላይ የ $10 ሚሊየን ዶላርስ መቀጮዎችን ጥሏል።

በ 6,200 ግለሰቦች ላይ የ $1,652 መቀጮዎች፤ እንዲሁም በሰባት ኩባንያዎች ላይ $9,913 በድምሩ $10,311,791 መቀጮዎች ተጥለዋል።

ገደቦቹ ለማኅበራዊ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ምን ማለት ይሆናል?

ከሌሎች የተለየ ለውጥ አይኖረውም። ዛሬ ማምሻውን የ3000 ማኅበራዊ ቤቶች ነዋሪች የኮሮናቫይረስ ምርመራ እንደተጠናቀቀ ከነገ ጀምሮ እንደ ማንኛውም የሜልበርን ነዋሪ ገደቦቹ ይመለከቷቸዋል። በአካባቢው ተመድበው የነበሩ የፖሊስ ሠራዊት አባላት ለስድስት ነዋሪዎች አንድ ፖሊስ ልዩ ጥበቃም ያከትማል። 

 


Share

Published

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends