በኒው ስውዝ ዌልስ 681 ሰዎች በማህበረሰብ ውስጥ በተዛመተ የኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሲሆን የአንድ ሰው ህይወትም አለፈ የተጣለውም ገደብ ተራዘመ ።
ከተያዙት መካከልም የ170 ያህሉ መንጩ የታወቀ ሲሆን የተቀሩት 511 የሚሆኑት ምንጭን ለማወቅ በምርመራው ቀጥሏል ።
በ80ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ አንድ ሰው ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ቀደም ሲልም የመጀመሪያውን ክትባት ወሰደውም እንደነበረ ተገለጥጥጿል። ግለሰቡ በሌላ አስጊ በሚባል የጤና ጠንቅ ሳቢያ ክትትል ሲደረግላቸውም ነበር ።
የኒው ሳውዝ ዌልስ ፕሪምየር ግላዲስ በርጂክልያን የተጣለው ገደብም እስከ ኦገስት 28 ደረስ መራዘሙን ተናግረዋል ።