ለኮቪድ - 19 ተስፋ ሰጪ መድኃኒት ተገኘ

ሳይንቲስቶች ሰሞኑን ውጤቶቹ ተስፋ ሰጪ የሆነው የኮቪድ - 19 መከላከያ መድኃኒት ርካሽና በሰፊው ሊዳረስ የሚችል መሆኑን እየገለጡ ነው።

Promising results shown by common steroid drug against COVID-19

Packages of Dexamethasone on display in a pharmacy Source: AAP

የእንግሊዝ ተመራማሪዎች መድኃኒቱ ርካሽና በሰፊው ተዳራሽ ከመሆኑም ባሻገር በፅኑ የታመሙ በሽተኞችን ሞት በአንድ ሶስተኛ ቀናሽ ሰለመሆኑም ተናግረዋል።

ጥናቱ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በጥብቅ የተካሔድ ሲሆን፤ ዴክሳሜታዞን ተብሎ የሚጠራውን አዲሱን መድኃኒት ከሁለት ሺህ በላይ [[2014]] የኮቪድ - 19 ሕሙማን እንዲታከሙበት ተደርጓል። በውጤቱም ከሁለት ጊዜ በላይ 4321 ከሆኑ መደበኛ ክብካቤ ብቻ ከሚያገኙ ሕሙማን እኩል ለመነጻጸር በቅተዋል።  

ውጤቱ የላቀ ስለመሆኑ ጥናቱን ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከሚመሩት አንዱ የሆኑት ዶ/ር ማርቲን ላንድሬይ ሲናገሩ፤

 [["ዴክሳሜታዞን የመተንፈሻ መሳሪያዎችን መጠቀም ግድ ይላቸው ከነበሩ ፅኑ ሕሙማን ውስጥ አንድ ሶስተኛ ያህሉን ከሞት መታደግ ችሏል። እንዲሁም፤ ለመተንፈስ የመተንፈሻ መሳሪያዎችን የማያስፈልጋቸውን ግና ሆስፒታል ውስጥ ሆነው ኦክሲጅን ማግኘት ከሚያሻቸው ውስጥ አንድ - አምስተኛ ያህሉን እንዲያገግሙ አድርጓል። እኒህ እንዲህ ላለ በሽታ ትልቅ ውጤቶች ናቸው"]] ብለዋል።  

በኒው ዮርክ የስሏን-ከተሪንግ ካንሰር ማዕከል የጤና ፖሊሲ ተጠባቢ የሆኑት ዶ/ር ፒተር ባኽ፤ ዴክሳሜታዞን ኮቪድ - 19ኝን በመከላከል ረገድ አንድ ግዙፍ እርምጃ ወደፊት እንደሆነ ገልጠዋል።

በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከስምንት ሚሊየን ያለፈ ሲሆን፤ ሩብ ያህሉ ተጠቂዎች የሚገኙት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ነው።

ቫይረሱ ላቲን አሜሪካ ውስጥ በስፋት እየተስፋፋ ይገኛል። ከ80 ሺህ በላይ ሰዎችን አጥቅቷል።

 

 

 

 

 


Share

Published

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends