አንድ ዕድሜው ከሁለት ዓመት በታች የሆነ ሕፃን ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ ሕይወቱ በኮሮናቫይረስ አለፈች

*** ብሔራዊ ካቢኔ ለ "ቅርብ ንኪኪ" አዲስ ትርጓሜ ይሁንታን ቸረ

COVID-19 update

Scott Morrison announces the reset of the 'close contact' criteria Source: AAP

ደቡብ አውስትራሊያ 1374 ነዋሪዎቿ በኮቪድ-19 መያዛቸውን ባስታወቀችበት በዛሬዋ ዕለት በኮሮናቫይረስ የተጠቃ የአንድ ሕፃን ልጅ ሕይወት አልፏል።

ፕሪሚየር ስቴቨን ማርሻል ሕፃኑ ገና ሁለት ዓመት ያልሞላው እንደነበር ገልጠው፤ አሟሟቱን አስመልክቶም ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል።  

አቶ ማርሻል ዕድሜያቸው ከአምስት እስከ አሥራ አንድ ያሉ ልጆች ከጃኑዋሪ 10 ጀምሮ የመጀመሪያ ዙር ክትባታቸውን መከተብ እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።

ብሔራዊ ካቢኔ

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ዛሬ ሐሙስ ዲሴምበር 30 ከቀትር በኋላ የኮቪድ-19 የቅርብ ንኪኪ ብሔራዊ ትርጓሜን አስመልክቶ የብሔራዊ ካቢኔው ከስምምነት ላይ መድረሱን ገለጡ። 

በዚህም መሠረት፤

  • የቅርብ ንኪኪ ማለት በተለየ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር፤ በአንድ ቤት ነዋሪ ከሆኑ ግለሰቦች ውስጥ አንዱ በኮቪድ 19 መያዙ ከተረጋገጠ ቤተኛ ጋር፣ ከቤት ውጪ ባሉ ቤቶች ወይም የክብካቤ ተቋም ውስጥ ከአራት ሰዓታት በላይ አብሮ ያሳለፈ 

  • በቅርብ ንኪኪነት የተፈረጀ ግለሰብ በበሽታው መያዙ ባይሰማውም እንኳ rapid antigen test (RAT) ምርመራ ሊያደርግ ይገባል

  • በRAT ፈጣን ምርመራ ውጤት ከቫይረስ ነፃ መሆኑን ከታወቀ በቫይረስ መያዙ ለተረጋገጠ ግለሰብ ተጋላጭ ከሆነባት ዕለት ጀምሮ ለሰባት ቀናት ራሱን  አግልሎ ሊቆይና በስድስተኛው ቀንም የRAT ፈጣን ምርመራ ሊያደርግ ይገባል

  • በRAT ፈጣን ምርመራ ውጤቱ በቫይረስ መያዙን ካመለከተ ግና የPCR ላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል

  • በቫይረስ የመያዝ ምልክቶችን የሚያሳይ ከሆነ የግድ የPCR ላቦራቶሪ ምርመራ ሊያደርግና ለሰባት ቀናት ራሱን አግልሎ ሊቆይ ይገባል

  • አዲሱ ትርጓሜ ከዛሬ ዕኩለ ለሊት አንስቶ በኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያ፣ ኩዊንስላንድ፣ ደቡብ አውስትራሊያና የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ግብር ላይ ይውላል 

  • በጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጣ መሠረት አዲሱ ድንጋጌ በአሁኑ ወቅት ራሳቸውን አግልለው ባሉት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል  
  • ድንጋጌው ታዝማኒያ ውስት ከጃኑዋሪ 1 ጀምሮ ግብር ላይ የሚውል ሲሆን፤ ኖርዘርን ቴሪቶሪና ምዕራብ አውስትራሊያ በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ያስታውቃሉ

  • ደቡብ አውስትራሊያ ምንም እንኳ አዲሱን ድንጋጌ ብትደግፍም ተገልሎ የመቆያ ጊዜን ሰባት ቀናት መሆኑን ከመቀበል ይልቅ 10 ቀናት እንዲሆን ወስናለች

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 12,226  ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።

ቪክቶሪያ ውስጥ 5,137 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 13 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

 ኩዊንስላንድ 2,222፣ ታዝማኒያ 92 ሰዎች ተጠቅቶባቸዋል።

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ .

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

 የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ 

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  


 


Quarantine and restrictions state by state:


Share
Published 30 December 2021 7:33pm
By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends