ብሔራዊ የዕርቅ ሳምንት 2022፤ አይበገሬ ይሁኑ - ለውጥ ያስገኙ

የብሔራዊ ዕርቅ ሳምንት ሁሉም አውስትራሊያውያን ከአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ጋር ማለፊያ ግንኙነት በመገንባት ለአገሪቱ ዕርቅ አስተዋፅዖ የሚያደርጉበት ጊዜ ነው።

Community

Source: Getty

አንኳሮች

  • የ2022 ብሔራዊ ዕርቅ ሳምንት መሪ ቃል 'አይበገሬ ይሁኑ፤ ለውጥ ያስገኙ' የሚል ነው። 
  • ዕርቅ አውስትራሊያና የአውስትራሊያ ፌዴራል ዘውጌ ማኅበራት አዲስ ሠፋሪ ማኅበረሰባት በብሔራዊ ዕርቅ ሳምንትና ከዚያም ባሻገር በዕርቅ ሂደቱ ወቅት ተሳታፊ እንዲሆኑ ያበረታታሉ። 
  • በብሔራዊ ዕርቅ ሳምንት የኩነት ቀን መቁጠሪያ ላይ የራስዎን ኩነቶች ማስፈርና በመላ አገሪቱ ያሉትንም ኩነቶች ዝርዝር ፈልገው ማግኘት ይችላሉ።

ብሔራዊ የዕርቅ ሳምንትን የምናከብረው ለምንድነው?

ብሔራዊ የዕርቅ ሳምንት የሚከበረው ሜይ 27 1967  ሕገ መንግሥቱን ለማሻሻል አውስትራሊያውያን በነቂስ ወጥተው የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ ለሰጡበት ቀን መታሰቢያነት ነው። ይህም የሕዝብ ቆጠራን ጨምሮ የአውስትራሊያ መንግሥት ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ድንጋጌዎችን እንዲደነግግ አስችሏል። 

እንዲሁም ሜይ 3,1992 የአቦርጂናልና ቶረስ ደሴት መሽመጥ ደሴት ሰዎች ባሕላዊ የመሬት ባለቤቶች ስለመሆናቸው ዕውቅና በመቸር የከፍተኛ ፍርድ ቤት የማቦ ብይን ያሳለፈበትን ያካተተ መታሰቢያ ነው። 

እኒህ ቀናት ብርቱ ወደ ዕርቅ መምሪያ መንገድ ነጥቦች ናቸው። 

የእዚህ ዓመት መሪ ቃል ምንድነው?

የ2022 ብሔራዊ ዕርቅ ሳምንት መሪ ቃል 'አይበገሬ ይሁኑ፤ ለውጥ ያስገኙ' የሚል ነው። 

'አይበገሬ ይሁኑ፤ ለውጥ ያስገኙ’ ለመላ አውስትራሊያውያን ዕልባት ላላገኘው ዕርቅን አንስቶ ለውጦችን በማስገኘት ሁላችንንም እንደ አገር የትሩፋቱ ተጋሪ የማድረግ መፈተኛ መጠይቅ ነው።
News
Source: Reconciliation Australia
የሰሜናዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ባንድጃላንግ ሴት የሆኑት የዕርቅ አውስትራሊያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ካረን ማንዲን ዕርቅ የእያንዳንዱ አውስትራሊያውያን ኃላፊነትና ንቁ ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል።   

“ብሔራዊ የዕርቅ ሳምንት ለሁላችንም ለአፍታ ስለ ግንኙነቶቻችን ቆም ብለን ማሰቢያ፣ አጉልተን ማሳያ፣ አዲስ መነጋገሪያ መክፈቻና ሁሉንም ማኅበረሰባት በኩነቶች ላይ እንዲሳተፉ ወይም የእንቅስቃሴዎች አካል እንዲሆኑ ማድረጊያ ጊዜ ነው” ሲሉ ለSBS ራዲዮ ገልጠዋል።

የአዲስ ሠፋሪዎች የብሔራዊ ዕርቅ ተሳትፎ

መሐመድ አል-ከሃፋጂ የአውስትራሊያ ዘውጌ ማኅበረሰባት ምክር ቤቶች ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ ሁሉም አዲስ ሠፋሪ ማኅበረሰባት በዕርቅ ሂደቱ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። 

በነባር ዜጎች፣ መጤዎችና የስደተኛ ማኅበረሰባት ዘንድ ያሉ አዎንታዊና አሉታዊ ገጠመኞችን ማንሳት አንዱ ማለፊያ መነሻ እንደሆነ ሲያመላክቱ፤

“ታሪክን ማወቅ፣ ማኅበረሰባቱ በምን ሁኔታዎች ውስጥ እንዳለፉ መረዳት የእኛ ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ምክንያቱም፤ ተመሳሳይ ተሞክሮዎችና ተመሳሳይ የለውጥ ፍላጎትች አሉንና” ብለዋል።
"ሁለታችንም ዘረኝነት ደርሶብናል፣ ሁለታችንም ኢ-ፍትሐዊነት ገጥሞናል፤ እናም ሁለታችንም የዚህች አገር እኩልነት ተጋሪ መሆን እንሻለን።"
ሁሉም መጤዎች የብሔራዊ ዕርቅ ሳምንትን ፋይዳ አይረዱም። 

በርካታ ሰዎች እንደምን ከአቦርጂናላ ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ጋር ባሕሎችንና ታሪኮችን አስመልክተው መነጋገር እንዳለባቸው ወይም የራሳቸውን የተሳትፎ ድርሻ አያውቁም።

የተሳትፎ ማበረታቻ መምሪያ

በ2020 የአውስትራሊያ ዘውጌ ማኅበረሰባት ምክር ቤቶች የተሳትፎ ማበረታቻ፤ ለመድብለባህል ድርጅቶች የዕርቅ ተሳትፎ ማበረታቻ መምሪያ በሚል ርዕስ አንድ የተሳትፎ መምሪያ አውጥቶ ነበር። 

የምክር ቤቶቹ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መሐመድ አል-ከሃፋጂ ዶክሜንቱ በብሔራዊ ዕርቅ ሳምንትና ከዚያም ባሻገር ለመነጋገሪያ ነጥብ መጀመሪያነት ማለፊያ እንደሆነ አመላክተዋል። 

የተሳትፎ ማበረታቻ መምሪያ የተወሰኑ ረብ ያላቸው እንቅስቃሴዎችን ይጠቁማል፤

  • የዕርቅ ድርጊት ዕቅድ ይንደፉ
  • በብሔራዊ ዕርቅ ሳምንት ተሳትፎ ያድርጉ
  • የናይዶክ ሳምንትን ያክብሩ
  • በአካባቢዎ ያሉ የነባር ዜጎች አረጋውያን እንኳን ወደ አገራችን መጣችሁ ወይም የጭስ ማጠን ሥነ ሥርዓትን እንዲያከናውኑላችሁ ጋብዙ
  • የሥራ ቦታዎ ባሕላዊ ብቃት ያለው እንዲሆን ጥረት ያድረጉ
 የአውስትራሊያ ዘውጌ ማኅበረሰባት ምክር ቤቶች የተሳትፎ ማበረታቻ መምሪያን እዚህ ያግኙ .
Community
Joan Baker watches Kevin Rudd deliver the National Apology to members of the Stolen Generations. Source: Getty

የዕለት ተዕለት አይበገሬነት

በዚህ ዓመት መሪ ቃል 'አይበገሬ ይሁኑ፤ ለውጥ ያስገኙ' መሪ ቃል መሠረት እያንዳንዱ ሰው በሁሉም ዘርፍ በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ውስጥ አይበገሬ ድርጊቶችን እንዲተገብሩ ዕርቅ አውስትራሊያ ጥሪ ያደርጋል። 

“ምናልባትም በዚህ ጉዳይ ላይ የእርስዎን አተያይ ከማይጋሩ ወዳጆችና ቤተሰብ ጋር አዋኪ የሆነ ውይይት ለማድረግ ጊዜው አሁን ይሆናል” ሲሉም ካረን ማንዲን ያበረታታሉ።

በብሔራዊ ዕርቅ ሳምንት ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ ማኅበራዊ ሚዲያዎንና የኢሚል ምስሎችን የመቀየር ያህል ቀላል ነው። በአካባቢዎ የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎችን ለመረዳት የ  ወይም ፊልሞችንና ፖድካስቶችን ለማግኘት የSBS ድረገፆችን ይጎብኙ።  

የእዚህን ዓመት የብሔራዊ ዕርቅ ሳምንት ኩነቶችን የያዘ ቀን መቁጠርያን እዚህ ያግኙ .

ለኮምፒዩተርዎ፣ ድረገጽዎ ወይም ማኅበራዊ ሚዲያዎ የብሔራዊ ዕርቅ ሳምንት ዲጂታል ምንጮች እዚህ ያግኙ .
Community
شعار أسبوع المصالحة الوطنية لعام 2022 Source: Reconciliation Australia/Tori-Jay Mordey/Carbon Creative

Share

Published

By Melissa Compagnoni
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends