በእኒህ ጊዜያት ውስጥም የቪክቶሪያ ፖሊስ አካላዊ ርቀትንና ወሸባ ገብቶ የመቆየት ድንጋጌዎችን የማስፈጸም ሥልጣኑን ይጠቀማል።
ይህንንም ለማከናወን 500 የፖሊስ ሠራዊት አባላት ይሠማራሉ።
ድንጋጌዎቹን ተላልፈው የሚገኙ ግለሰቦች እስከ $1,652 የንግድ ተቋማት እስከ $9,913 መቀጮ ይጣልባቸዋል።
ይህንንም ጥሰው የሚገኙ ግለሰቦች፤ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረ ፍርድ ቤት ቀርበው እስከ $20,000 ኩባንያዎች እስከ $100,000 ዶላርስ ይቀጣሉ።
የቪክቶሪያ መንግሥት መልዕክቱን በድጋሚ አበክሮ ሲያስገነዘብ "አካላዊ ርቀትን ጠብቁ። ከመጨባበጥና መተቃቀፍ ተቆጠቡ። ሥነ ንጽሕናን በመጠበቁ ቀጥሉ። ምግብና መጠጥን ተጋርታችሁ አትመገቡ፤ አትጠጡ። ጤና ካልተሰማችሁ ከቤት አትውጡ፣ ጓደኞችና ቤተሰቦችን ሔዳችሁ አትጠይቁ፣ ሽርሽር አትሂዱ፣ ወደ ሥራ አትግቡ፣ ቤት ውስጥ ቆዩ" ብሏል።