የኢትዮጵያ ከፍተኛ የሚሊተሪ ኮማንደር እና በጦርነት በከፍተኛ የተጎዳው የትግራይ ክልል ያልተከለከሉ የሰብአዊ እርዳታዎች ወደክልሉ እንዲገቡ ተስማሙ።
ይህ የሆነውም በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የተፈረመውን ስምምነት ተከትሎ ሲሆን ፤ሂደቱ ወደ የሰላሙ ስምምነት በተግባር እንዲውል መንገድ እንደሚዘረጋ ተነግሮለታል ።
የኢትዮጵያ ከፍተኛ የወታደራዊ ኮማንደር እና በጦርነት የተጎዳው የትግራይ ክልል ያልተከለከሉ የሰብአዊ እርዳታዎች ወደክልሉ እንዲገቡ የተስማሙ ሲሆን የህም የሆነው ባለፈው ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላእና በጋራ በተቋቋመው የትጥቅ አስፈቺ ኮሚቴ አማካኝነት ነው።
በአፍሪካ ህብረት የተመራው እና በኬንያ እየተካሄደ ያለውት ውይይት ፤ በሁለቱ መካከል የነበረው ጦርነት እንዲቆም ፤ በኢትዮጵያ እና በህወሃት መሪዎች መካከል ባለፈው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ የተፈረመውን ተከትሎ ነው።
ሁለቱም ወገኖች የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና በክልሉ ለሚኖሩ ከ5 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ለሚሆኑት ዜጎች የሰብአዊ እርዳዎች እንዲገቡ ተስማምተዋል ።
በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞው የናጄሪያው ርእሰ ብሄር ኦሉሴንጎን ኦባሳንጆ እንዳሉት በጦርነቱ የተጎዱትን ሰላማዊ ዜጎች ለመታደግ የተወሰደው እርምጃ ከፍተኛ የሚባል ነው።
“ያስመዘገብነው ውጤት የሰብአዊ እርዳታን ያለገደብ እንዲገባ መፈቀዱ እና ተግባራዊነቱም በፍጥነት የሚውል መሆኑ፤ ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ እና የጦር መሳሪያን በማስፈታት ረገድም እየተሄደበት ያለው ጎዳና እንዲሁም ሰላም እና ጸጥታን ለማስከበር የሚደረገው ጥረት አመርቂ ውጤትን እያስመሰከረ ነው። ” ብለዋል።
በስምምነቱ መሰረትም የትጥቅ ማስፈታቱ ሂደት እና የውጭ አገር ማለትም ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ወታደራዊ ሀይሎችን ከትግራይ ከልል ከማስወጣት ሂደቱ ጋር መሳ ለመሳ የሚሄድ ይሆናል ።
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንዳረጋገጡትም በኢትዮጵያ ወታደራዊ ሀይል ትእዛዝ የሰብአዊ እርዳታዎችን ለአብዛኛው የትግራይ ክልል ለማዳረስ የተደረጉ ጥረቶችን ለማረጋገጥ ተችሏል።
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የኢትዮጵያ ኢታማጆር ሹም እንዳሉት “ ለህዝባችን እና ለአገራችን ሰላም እና ደህንነትን ለማምጣት ሙሉ ቁርጠኛነታችንን ማረጋገጥ እንወዳለን ፤ ስለዚህ የፕሪቶርያውን ስምምነት እና ድንጋጊ በተግባር ለማዋል ዝግጁ ነን ።” ብለዋል
በትግራይ የተቀሰቅሰው ግጭት በጥቅምት 2013 ሲሆን የህወሀት መራሹን ጦር በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ በነበረው የመንግስት የጦር ሀይል ላይ ጥቃት ፈጽሟል በሚል ክስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጦር ሀይሉን በማዘዛቸው እደሆነ ይታወሳል።
ጦርነቱም ከተጀምረ ወዲህ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ነዋሪዎች በምግብ እጥረት የተጎዱ ሲሆን በተጨማሪም የመሰርታዊ ተቋማት እንደ መብራት ፤ ስልክ እና የባንክ አገልግሎቶችን በብቃት ማዳረስ አልተቻለም ።
ለወራት ሰፍኖ የነበረው አንጻራዊ የሰላም አየር በሺህ የሚቆጠሩ እርዳታን የጫኑ ከባድ መኪኖች ወደ ትግራይ ክልል እንዲገቡ ያስቻለ ቢሆንም ፤ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰ የተነገረለት ጦርነት በነሓሴ ወር እንደገና መቀስቀሱ ይታወሳል።
ጀነራል ታደሰ ወረደ የህወሃት ከፍተኛ መሪ በበኩላቸው እንደተናገሩት
“ ባለፉት ሁለት አመታት ከፍተኛ የሆነ ሀዘንን አስተናግደናል አሁንም እንደዚሁ ፤ ዛሬ የምናደርገው ስምምነት የህዝባችንን እንግልትን በፍጥነት ያቆማል በሚል ተስፋ ነው ። ” ብለዋል
በአፍሪካ በህዝብ ብዛት በሁለተኛ ተርታ ባለችው አገር በሁለቱም ወገኖች ላይ የደረሰው ጥቃት የተመዘገበ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችም ከቀዬአቸው ተፈናቅናዋል ።
ባለፈው ነሐሴ ወር የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዋና ሀላፊ ቴዎድሮስ አድሀኖም ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ደርጃ በጦርነት ለተጎዳችው የትግራይ ክልል የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት እንዳይሰጥ ዘረኝነት እና መድልዎ ምክንያት ሆነዋል ብለው መናገራቸው ይታወሳል ።