ቪክቶሪያ የኮሮናቫይረስ ገደቦቿን አላላች

*** ቪክቶሪያ ከዛሬ ማክሰኞ 11:59pm ጀምሮ ለአምስተኛ ጊዜ ጥላ የነበረቻቸውን የኮቪድ-19 ገደቦች ታረግባለች፤ ሆኖም ለቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት የተቀሩት ገደቦች ፀንተው ይቆያሉ

SBS Amharic

Source: SBS Amharic

ከዛሬ ዓርብ ጁላይ 27 ዕኩለ ለሊት ጀምሮ ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው የኮሮናቫይረስ ገደብ ይላላል። 

በዚህም መሠረት፤

ማኅበራዊ

  • ከቤት ለመውጣት ምክንያቶች አያሻዎትም
  • የ 5 ኪሎ ሜትር ገደቦች ተነስተዋል፤ የፈለጉትን ያህል ርቀት መጓዝ ይችላሉ
የፊት ጭምብሎች

  • የፊት ጭምብሎችን ከመኖሪያ ቤት ውጪ አጥልቆ መንቀሳቀስ ይቀጥላል
ትምህርት ቤቶች

  • ትምህርት ቤቶች ክፍት ይሆናሉ፤ ከ12 ዓመት ዕድሜና በላይ ያሉ ተማሪዎች የፊት ጭምብል ማጥለቅ ግድ ይሰኛሉ 
መሥሪያ ቤቶች

  • ከ25 ፐርሰንት ያልበለጡ ሠራተኞች በየሥራ ገበታቸው መሰማራት ይችላሉ
  • ሁሉም የሥራ ሥፍራዎች የኮቨድጥንቃቄ ዕቅድ ግብር ላይ ማዋል ይጠበቅባቸዋል
የመስተግዶ ግልጋሎት ሰጪዎች

  • ከ100 ያልበለጡ ደንበኞቻቸውን ተቀምጠው እንዲስተናገዱ ማድረግ ይችላሉ።

  • በቡድን ከ10 ሰዎች በላይ ማስተናገድ አይቻልም።

  • ለአንድ ሰው የአራት ስኩየር ሜትር ርቀት የተጠበቀ ይሆናል። 

  • ችርቻሮና እንደ የውበት ሳሎንና ፀጉር ማስተካካያ የመሳሰሉ ግልጋሎት ሰጪዎች ክፍት ሆነው ግልጋሎቶቻቸውን መስጠት ይችላሉ

የአካል እንቅስቃሴና መዝናኛዎች

  • የቀጥታ የመድረክ ሙዚቃ፣ የአካል እንቅስቃሴና ዳንስ ለአንድ ሰው የአራት ስኩየር ሜትር ርቀት በጠበቀ ሁኔታ ክፍት ሆነው ደንበኞቻቸውን ማስተናገድ ይችላሉ 
  • በቤት ውስጥ ከ100 ከቤት ውጪ ከ300 በላይ ሰዎችን ማስተናገድ አይችሉም
  • የማኅበረሰብ ስፖርት ተመልካቾችን ሳያካትት መቀጠል ይችላል
  • የበረዶ መንሸራተት መስኮች ክፍት ይሆናሉ፤ ተጠቃሚዎች ወደ ሥፍራው ከመድረሳቸው በፊት ከኮቪድ-19 ነፃ የመሆናቸውን የምርመራ ማረጋጋጫ ሊያቀርቡ ይገባል 
ልዩ ሥነ ሥርዓቶች

  • በሠርግና የቀብር ሥነ ሥርዓቶች ላይ በቤት ውስጥና በውጭ እስከ 50 ዕድምተኛና ለቀስተኞች መገኘት ይችላሉ 
  • ቤተ እምነቶች በቤት ውስጥ እስከ 100 ከቤት ውጪ ከ300 ላልበለጡ ምዕመናን ግልጋሎቶቻቸውን መስጠት ይችላሉ
 የተጨማሪ ገደቦች መነሳት ከሁለት ሳምንት በኋላ ይገለጣል።


Share
Published 27 July 2021 2:37pm
Updated 27 July 2021 2:42pm
By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends