በቪክቶሪያ 57 ሰዎች በማህበረሰብ ውስጥ በተዛመተ የኮሮናቫይረስ ተጠቁ ።
ይህ ቁጥርም የሁለተኛው ዙር የቫይረስ ስርጭት ከታየ በኋላ ከፍተኛ የሚባል እንደሆነ ተነግሯል ።
የጤና ዲፓርትመንት እንዳሳወቀው አዲስ ከተመዘገቡት ውስጥም 54ቱ በቅርቡ ከታየው ወረርሽኝ ጋር የሚገናኙ ሲሆን 42 ያህሉም ራሰቸውን ለይተው ያስቀመጡ ናቸው ።የተቀሩቱ ሶስቱ ምንጫቸው እስካሁንም አልታወቀም ።
የቪክቶሪያው ፕሪምየር ዳናኤል አንድሪውስ እንዳሉት ከ 44 ቱ ውስጥ 41 ያህሉ በሚያስተላልፉበት ወቅት በለይቶ ማቆያ የነበሩ ሲሆን በ13ተኛ ቀናቸውም እንደገና ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
ስለሆነም ሁሉም እንደገና ራሳቸውን ለይተው ማቆየት ይኖርባቸዋል ብለዋል ።