ቪክቶሪያ ዳግም የኮቪድ - 19 ገደቦችን ጣለች

ቪክቶሪያ በአንድ ቀን 25 አዲስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ካስመዘገበች በኋላ የላላውን ገደቦቿን አጥብቃለች።

Victorian Premier Daniel Andrews speaks to the media during a press conference at Treasury Theatre in Melbourne, Saturday, June 20, 2020. (AAP Image/Luis Ascui) NO ARCHIVING

Victorian Premier Daniel Andrews speaks to the media during a press conference at Treasury Theatre in Melbourne, Saturday, June 20, 2020. (AAP Image/Luis Ascui) Source: AAP

የቫይረሱ በሁለት ዲጂት ከፍ ማለት ምናልባትም የሁለተኛ ዙር ወረርሽኝ እንዳይቀሰቅስ ሥጋት አሳድሯል።

ከኤፕሪል መጨረሻ ወዲህ ከግማሽ በላይ አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከቤተሰብ ወደ ቤተሰብ በተዛመተ ተጋቦት ነው። 

የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ ገደቦቹን እንደገና ስለ ማጥበቁ አስፈላጊነት ሲናገሩ፤

"ራሳችሁን አግልሉ ከተባላችሁ የግድ ማግለል አለባችሁ። የራሳችሁን ውሳኔ መወሰን አትችሉም። ምክንያቱም ይህ በግላችሁ የምትወስኑት ውሳኔ አይደለምና። የተቀረውን ቪክቶሪያ ለተጋላጭነት ትዳርጋለችሁ። ያ ትክክል አይደለም። ተገቢ ተግባርም አይሆንም። እኒህ እርምጃዎች አስፈላጊ ናቸው። አዋኪም ቢሆኑ ያስፈልጋሉ" ብለዋል።

በዚህም መሠረት ከእሑድ ጁን 21 እኩለ ለሊት ጀምሮ እስከ ጁላይ 12፤

  • ቪክቶሪያውያን ቤታቸው ውስጥ ተቀብለው ሊስተናግዱ የሚችሉት ከአምስት ሰዎች አይበልጥም
  • ከቤት ውጪ ቤተሰቦችና ጓደኞች ከ10 በላይ መሰባሰብ አይችሉም
  • ምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ የጨረታ አዳራሾች፣ ቤተ መጽሐፍት፣ ሙዚየሞችና የእምነት ቤቶች ከ20 የበለጡ ሰዎችን አያስተናግዱም
  • ሰኞ ዕለት በሮቻቸውን ለመክፈት በዕቅድ ላይ ያሉ የአካል እንቅስቃሴ ማጠንከሪያ ሥፍራዎች፣ ሲኒማ ቤቶች፣ ቲያትር ቤቶችና የውርርድ ማኪያጃዎች በእቅዳቸው መሰረት መስተንግዶቻቸውን ለደንበኞቻቸው መስጠቱን መቀጠል ይችላሉ። ሆኖም ከ20 በላይ ሰዎችን ማስተናገድ አይፈቀድላቸውም
  • የማኅበረሰብ ስፖርት - የልጆችና አካላዊ ንኪኪ የሌላቸው የአዋቂዎች ስፖርት እንቅስቃሴዎች በዕቅዳቸው መሠረት መቀጠል ይችላሉ  
  • የበረዶ መንሸራተትና የመኝታ ግልጋሎቶች ሲጪዎች ተጨማሪ የጥንቃቄ ደንቦችን ተግባራዊ ባደረገ መልኩ ደንበኞቻቸውን ማስተናገድ ይችላሉ 
የቪክቶሪያ ዋና የጤና ኃላፊ ፕሮፌሰር ብሬት ሳቶን ቀውሱ እንዳይባባስ ሊወሰዱ የሚገቡ እርምጃዎችን አስመልክቶ ቪክቶሪያ በመስቀለኛ መንዶች ላይ መሆኗን ጠቅሰዋል። 

 በጤናቸው ሳቢያ ቫይረሱን ላለማስፋፋት ቤታቸው ለሚቆዩ ግለሰቦች የ1,500 ዶላርስ ክፍያው ይቀጥላል።

ፕሪሚየር አንድሩስ፤ ለቪክቶሪያውያን በሰጡት ማሳሳቢያ "አካላዊ ርቀትን ጠብቁ። ከመጨባበጥና መተቃቀፍ ተቆጠቡ። ሥነ ንጽሕናን በመጠበቁ ቀጥሉ። ምግብና መጠጥን ተጋርታችሁ አትመገቡ፤ አትጠጡ። ጤና ካልተሰማችሁ ከቤት አትውጡ፣ ጓደኞችና ቤተሰቦችን ሔዳችሁ አትጠይቁ፣ ሽርሽር አትሂዱ፣ ወደ ሥራ አትግቡ፣ ቤት ውስጥ ቆዩ" ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ የኢሰንደን እግር ኳስ ተጫዋች ኮኖር ማክኪና በኮቪድ - 19 በመያዙ የአውስትራሊያ እግር ኳስ ሊግ ቡድናት ሥጋት ገብቷቸዋል።

በዚህም የተነሳ እሑድ ጁን 21 ኢሰንደንና ሜልበርን ዲመንስ ሊያካሂዱት የነበረው ሶስተኛ ዙር ግጥሚያ እንዳይካሔድ ተደረጓል።

 አውስትራሊያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች 102 ላይ ረግቶ ጸንቷል። በቫይትረሱ የተያዙ ሰዎች ቁትር 7400 ደርሷል። 

 ስለ ኮሮናቫይረስ በቋንቋዎ ወቅታዊ መረጃን ካሹ sbs.com.au/coronavirus ድረገጻችንን ይጎብኙ።


Share

Published

Updated

By Sonia Lal
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends