ከዛሬ ዓርብ ፌብሪዋሪ 26 ዕኩለ ለሊት ጀምሮ ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው ደረጃ ሁለት የኮሮናቫይረስ ገደብ ቅድመ የገና በዓል ወደ ነበረበት ይመለሳል።
በዚህም መሠረት፤
ማኅበራዊ
- ከቤት ለመውጣት ገደብ የለም
- በአደባባይ ለመሰባሰብ ከተለያዩ የቤተሰብ አባላት እስከ 100 ሰዎች መሰባሰብ ይችላሉ (ቁጥሩ ዕድሜያቸው ከ12 ወራት በታች የሆኑ ሕጻናትን አይጨምርም)
- በቀን ቁጥራቸው ከ30 ያልበለጡ ሰዎች ቤትዎ መጥተው ሊጎበኝዎት ይችላሉ (ቁጥሩ ዕድሜያቸው ከ12 ወራት በታች የሆኑ ሕጻናትን አይጨምርም) የቤትዎ ጓሮ ወይም በራፍ እንደ ቤት ይቆጠራል
የፊት ጭምብሎች
- የፊት ጭምብሎችን ማጥለቅ ግድ የሚሰኙት የሕዝብ ትራንስፖርት፣ ታክሲና ሌሎች በጋራ የሚጋሯቸው የትራንስፖርት አገልግሎቶች ሲጠቀሙ፤ የአረጋውያን መጠወሪያ ተቋማት፣ ትላልቅ የችርቻሮ ሱቆች፣ የገበያ አዳራሾችና ሱፐርማርኬቶች የመሳሰሉ የቤት ውስጥ መገበያያ ሥፍራዎች
ትምህርት ቤቶች
- ትምህርት ቤቶች፣ ሙዋዕለ ሕጻናትና የጎልማሶች መማሪያዎች ክፍት ሆነው ይቀጥላሉ
ሥራ
- ከ75 ፐርሰንት ያልበለጡ ሠራተኞች በየሥራ ገበታቸው መሰማራት ይችላሉ
- ሁሉም የሥራ ሥፍራዎች የኮቨድጥንቃቄ ዕቅድ ግብር ላይ ማዋል ይጠበቅባቸዋል
የአካል እንቅስቃሴና መዝናኛዎች
- የቤት ውስጥ የአካል እንቅስቃሴና የማኅበረሰብ ስፖርት ርቀታቸውን ጠብቀው ከ50 ሰዎች ሳይበልጡ መከናወን ይችላሉ
- ከቤት ውጪ የአካል እንቅስቃሴና የማኅበረሰብ ስፖርት ርቀታቸውን ጠብቀው ከ100 ሰዎች ሳይበልጡ መከናወን ይችላሉ
- የመዋኛ፣ የእንፋሎት ክፍሎችና ምንጮች ግልጋሎቶችን አንድ ሰው በአራት ስኩየር ሜትር ርቀት መጠቀም ይቻላል
ልዩ ሥነ ሥርዓቶች
- ሠርግ በውጭና ቤት ውስጥ ሲካሄዱ ማኅበራዊ ርቀት እንደተጠበቀ ሆኖ ገደብ አይኖራቸውም፤ የዕድምተኞች ኤሌክትሮኒክ ሬኮርድ ሊያዝ ይገባል። በግል መኖሪያዎች ሲካሄዱ ማኅበራዊ ርቀት እንደተጠበቀ ሆኖ ከ30 ዕድምተኞች ሊበልጡ አይገባም።
- ቀብር በውጭና ቤት ውስጥ ሲካሄዱ ማኅበራዊ ርቀት እንደተጠበቀ ሆኖ ገደብ አይኖራቸውም። የለቀስተኞች ኤሌክትሮኒክ ሬኮርድ ሊያዝ ይገባል። በግል መኖሪያዎች ሲካሄዱ ማኅበራዊ ርቀት እንደተጠበቀ ሆኖ ከ30 ዕድምተኞች ሊበልጡ አይገባም
- ቤተ እምነቶች በውጭና ቤት ውስጥ ሲካሄዱ ማኅበራዊ ርቀት እንደተጠበቀ የምዕመናን ኤሌክትሮኒክ ሬኮርድ ሊያዝ ይገባል (ሁኔታው ካልፈቀደ በወረቀት ላይ ማስፈር ግድ ይላል)