የቪክቶሪያ ኮሮናቫይረስ ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ - ደረጃ 4 ገደብ ለሁለት ሳምንታት ተራዘመ

*** የሰዓት ዕላፊ ገደብ እስከ ሴፕቴምበር 26 ይጸናል

Victoria's road map

Source: AAP

የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ ዛሬ እሑድ ሴፕቴምበር 6 - 2020 የሜልበርንና ሪጂናል ቪክቶሪያ የኮሮናቫይረስ ገደቦች ማላሊያ ፍኖተ ካርታን ያፋ አድረገዋል።

በዚህም መሠረት የሜልበርን ደረጃ 4 ገደቦች እስከ ሴፕቴምበር ወር መጨረሻ ተራዝሟል።

በሁለቱ ሳምንታት የደረጃ 4 ገደቦች ማራዘሚያ ወቅት እስከ ሴፕቴምበር 13 ከ8pm-5am ተጥሎ ያለው ሰዓት ዕላፊ ገደብ ከሴፕቴምበር 14 ጀምሮ ከ9pm-5am ተራዝሞ ይቀጥላል።  

ፕሪሚየር አንድሩስ የገደቦቹን መራዘም አስመልክቶ ሜልበርናውያንን ይቅርታ የጠየቁት ሲሆን ለማራዘም ግድ የተሰኙትም ለጊዜው ብቸኛው አማራጭ ይኼው ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የማንሰራሪያ ፍኖተ ካርታ የሜልበርንና ሪጂናል ቪክቶሪያ ገደቦች አነሳስ ለየቅል ናቸው።

በዕቅዱ መሠረት የዳታ ውጤቶችን ተመርኩዞ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ቤተሰብ የበጋ ዕረፍት የሚያደርጉበትና ወደ ውቅያኖስ ዳርቻ መጓዝ ክፍት ይሆናል። 

ይሁንና ዕቅዱ ግብር ላይ የሚውለው ደረጃ በደረጃ ሲሆን በመጀመሪያው ደረጃ ላጤዎችና ላጤ እናቶችን ቤታቸው በመዝለቅ አንድ ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል መጥቶ ሊጎበኛቸው ይችላል።

አሁን ያለው የአንድ ሰዓት አካላዊ እንቅስቃሴ በደረጃ አንድ በቀን ወደ ሁለት ሰዓት ከፍ ይላል። ይህም በተከታታይ ለሁለት ሰዓታት አለያም በፈርቃ ለሁለት ጊዜ ሙሉ ሰዓት አካላዊ እንቅስቃሴ ማካሄድ ይቻላል።

አካላዊ እንቅስቃሴውን በሚያደርጉበት ወቅትም አብሮዎት ከሚኖር ወይም ከቤት ውጭ ካለ አንድ ሰው ጋር መሆን ይችላሉ።   

ማኅበራዊ ግንኙነትን በተመለከተም በአካባቢዎ ባሉ መናፈሻዎች ሽርሽር ማድረግን፣ በአካባቢዎ ባሉ የባሕር ዳርቻዎች መጽሐፍ ማንበብ ተካታች ሆነዋል።

ሴፕቴምበር 28 ከመዳረሱ በፊት በጤና ባለሙያ ቡድን የቫይረሱ መስፋፋት ደረጃ ይገመገማል። 

በደረጃ ሁለት ሽግግር ወቅት ሜልበርን ውስጥ የኮንስትራክሽን፣ ማምረቻ ፋብሪካዎች፣ የመናፈሻ ስነ-ገጽና በተናጠል የሚሰሩ ሠራተኞችን አካትቶ ወደ 100,000 የሚደርሱ ወደ ሥራ ገበታቸው ይመለሳሉ።

ችርቻሮና መስተንግዶን ከመሳሰሉ ከሌሎች ንግድ ተቋማት ጋር አሁን እስከ ሴፕቴምበር ተራዝመው ያሉት ገደቦች ከመጠናቀቃቸው በፊት እንደምን ወደፊት መራመድ እንደሚቻል ተከታታይ ውይይቶች ይካሄዳሉ።

ሙዋዕለ ሕጻናት ፈቃድ ግድ ሳይሉ ክፍት ይሆናሉ።

የሪጂናል ቪክቶሪያ ነዋሪዎች ከሴፕቴምበር 13 ክምሽቱ 11:59pm ጀምሮ ላጤዎችና ላጤ እናቶችን ቤታቸው በመዝለቅ ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል መጥቶ ሊጎበኛቸው ይችላል። 

ከቤት ውጪም እስከ አምስት ሰዎች በመናፈሻ፣ የባሕር ዳርቻ ከሁለት ቤተሰብ ባልበለጠ መገናኘት ይችላሉ።

ለሪጂናል ቪክቶሪያ የውጪ መጫዎቻ ሥፍራዎች ክፍት ይሆናሉ። እንዲሁም በውጪ እስከ አምስት ምዕመናንና አንድ የእመነት መሪን ጨምሮ ሃይማኖታዊ ግልጋሎቶችን ማከናወን ይችላሉ። 

ተማሪዎች በተርም አራት ደረጃ በደረጃ ወደ ትምህርት ቤት ይመለሳሉ።

 

 

 

 

 

 


Share
Published 6 September 2020 4:07pm
By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends