የቨርጂን አውስትራሊያ የበረራ አስተናጋጅ በኮሮናቫይረስ መያዝ ሶስት ክፍለ አገራትን በተጠንቀቅ አቁሟል

*** የመላ ሲድኒ ከተማ፣ ብሉ ማውንቴንስ፣ ማዕከላዊ ኮስትና ዎሎንጎግ ነዋሪች ለሆኑና መመዘኛዎችን ለሚያሟሉ እስክ $500 ድጎማ ይሰጣል።

Virgin Australia

Health authorities are scrambling to contact passengers on five flights after a Sydney-based Virgin cabin crew member tested positive to COVID-19. Source: Corbis News

አንድ የሲድኒ ቨርጂን የበረራ አስተናጋጅ ቅዳሜ ምሽት በኮሮናቫይረስ መያዝን ተከትሎ የጤና ባለ ስልጣናት የአምስት አውሮፕላን መንገደኞች የቫይረስ ምርመራ እንዲያደርጉ ለመንገር በጥድፊያ ላይ ናቸው።  

በአምስቱ በረራዎች ዓርብና ቅዳሜ መንገደኞቹ የተጓጓዙት ከብሪስበን፣ ሜልበርን፣ ሲድኒና ጎልድ ኮስት ወይም ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው ከተማ ነው።

በቫይረሱ የተያዘው/ችው የበረራ አስተናጋጅ በአሁኑ ወቅት ወሸባ ገብታለች/ገብቷል።  

ገደቦች

ከትናንት ቅዳሜ ከምሽቱ 6pm ጀምሮ እስከ ጁላይ 9 እኩለ ለሊት ድረስ ጸንቶ የሚቆይ የኮሮናቫይረስ ገደቦች በመላ ሲድኒ ከተማ፣ ብሉ ማውንቴንስ፣ ማዕከላዊ ኮስትና ዎሎንጎግ ላይ ተጥሏል። ገደቡ ሪጂናል ኒው ሳዝ ዌይልስንም ያካትታል።

ለሁለት ሳምንት የሚቆየው ገደብ የተጣለው የኒው ሳውዝ ዌይልስ ካቢኔ አስቸኳይ የቀውስ ስብሰባ ካካሔደ በኋላ ነው።

ገደቡን ተከትሎ ከቤት ለመውጣት የሚቻለው ለገበያ ሸመታና ግልጋሎቶች፣ የሕክምና ክብካቤ፣ ለኮሮናቫይረስ ክትባት፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ (በቡድን ከ10 ሰዎች ያልበለጡ) ከቤት ሆኖ ለመሥራት ወይም ለመማር ለማያስችሉ አስፈላጊ ለሆኑ ሥራዎችና ትምህርት ይሆናል። 

ከእሑድ ጁን 27 ከምሽቱ 11:59pm ጀምሮ የሠርግ ሥነ ሥር ዓት ማካሔድ የማይቻል ሲሆን፤ ቀብር ላይ ለአንድ ሰው በአራት ስኩየር ሜትር በተወሰነ ርቀት ከ100 ያልበለጡ ለቀስተኞች ሊታደሙ ይችላሉ። በቤት ውስጥ የፊት ጭምብል ማጥለቅን ግድ ይላል። 

የማኅበረሰብ ስፖርት የተጣሉት ገደቦች እስኪነሱ አይካሄድም። 

ሕጻናት ጨምሮ ቤተሰብን ለመጎብኘት ቁጥራቸው ከአምስት መብለጥ አይችልም። ከመኖሪያ ቤት ውጪ መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በውጪ የሚካሔዱ ኩነቶችን አክሎ የፊት ጭምብል ማጥለቅ ግዴታ ይሆናል። 

ፕሪሚየር ግላዲስ በርጂክሊያን የተጣሉት ገደቦች ላይ በሰባት ቀናት ውስጥ ክለሳ የሚደረግባቸው መሆኑን ገልጠዋል።

 የገንዘብ ድጋፍ

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፕሪሚየር ግላዲስ በርጂክሊያን ነዋሪዎች በፍርሃት ለሸመታ እንዳይዋከቡ ወይም የገንዘብ ድጋፍን አስመልክቶ እንዳይጨነቁ አሳስበዋል። ሱቆች ክፍት ሆነው እንደሚቆዩና የገንዘብ ድጎማም በመጪዎቹ ቀናት እንደሚደረግ ተናግረዋል።  

የአውስትራሊያ ምክትል የሕክምና መኮንን ፕሮፌሰር ማይክል ኪድ መላ ሲድኒ ከተማ፣ ብሉ ማውንቴንስ፣ ማዕከላዊ ኮስትና ዎሎንጎግ በኮሮናቫይረስ ዋነኛ ቀጣናነት በመፈረጃቸው በእዚያ አካባቢ ነዋሪ ለሆኑና መመዘኛዎችን ለሚያሟሉ እስክ $500 ድጎማ ይሰጣል።

 

 


Share
Published 27 June 2021 10:35am
By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends