የስደተኞች ሳምንት ምንድነው? አውስትራሊያ ውስጥ በየዓመቱ የሚከበረው ስለምን ነው?

የስደተኞች ሳምንት ስደተኞች ለአውስትራሊያ ስላበረከቷቸው ማለፊያ አስተዋፅዖዎች በየዓመቱ ለሕዝብ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ከፍ ያለ እንቅስቃሴ የሚካሔድበት ነው።

Refugees

Credit: Getty Images/bymuratdeniz

አንኳሮች
  • የስደተኞች ሳምንት ለሕዝብ ስለ ስደተኞች መረጃን ለመቸር ከፍ ያለ ዓመታዊ እንቅስቃሴ የሚከወንበት ነው
  • የስደተኞች ሳምንት በየዓመቱ የተለያየ ግንዛቤ የማስጨበጫ ቃል አለው
  • የአውስትራሊያ ስደተኞች ምክር ቤት ዓመቱን በሙሉ ስለ ስደተኞች ግንዛቤን ለማስጨበጥ በርካታ ፕሮግራሞችን ያካሂዳል
  • ባለፈው አንድ አሠርት ዓመት የስደተኞች ቁጥር ከእጥፍ በላይ ጨምሯል
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ለደኅንነታቸው ዋስትናን ፍለጋ ቀዬዎቻቸውን ይለቅቃሉ።

አውስትራሊያ ውስጥ የስደተኞች ሳምንት ሁሌም የሚውልበትን ጁን 20 አካትቶ ከእሑድ እስከ ቅዳሜ ተከብሮ ይሰነብታል።

የመጀመሪያው የስደተኞች ሳምንት ኩነቶች ሲድኒ ውስጥ የተካሔዱት በኦስትኬይር አማካይነት በ1986 ነው። በ1987 የአውስትራሊያ ስደተኞች ምክር ቤት የሳምንቱ ተባባሪ አዘጋጅ ሆነ። በዓመቱ ዝግጅቱ ብሔራዊ ኩነት ለመሆን በቃ። በ2004 ምክር ቤቱ የስደተኞች ሳምንት አዘጋጅነት ኃላፊነትን ተረከበ።

የአውስትራሊያ ስደተኞች ምክር ቤት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ አዳማ ካማራ የስደተኞች ሳምንት ዋነኛ ዓላማ ስደተኞች ለአውስትራሊያ ሕብረተሰብ ያበረከቷቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎችን ማክበር እንደሁ ያስገነዝባሉ።

Adama Kamara Deputy CEO RCOA
Adama Kamara, RCOA’s Deputy Chief Executive Officer. Credit: RCOA
ለእኛ አጠቃላይ ዓላማው በስደተኛ ማኅበረሰባትና የስደተኛ ማኅበረሰባት ባልሆኑት መካከል የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖርና አንዳችን አንዳችንን በበለጠ ተቀባይ እንድንሆን ማድረግ ነው።
አዳማ ካማራ፤ የአውስትራሊያ ስደተኞች ምክር ቤት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ

የስደተኞች ሳምንት ዓመታዊ ግንዛቤ ማስጨበጫ ቃል

የስደተኞች ሳምንት በየዓመቱ የሚቀየር አለው። ይህም የሚሆነው በመላው አውስትራሊያና በዓለም ዙሪያ ስደተኞችን የሚያውኩ ጉዳዮችን አስመልክቶ ግንዛቤ በመፍጠር ሰፊውን ማኅበረሰብ ስደተኝነት ምን እንደሚመስል ልብ ለማሰኘት ነው።

መሪ ቃሉ ወጥ የሆነና ያልተዛባ መልዕክትን በመላ አገሪቱ ለማሰራጨት የኝዛቤ ማስጨበጥ ዘመቻና እንቅስቃሴዎች ተፅዕኖን ለማጉላት ያስችላል።

የዓመታዊ መሪ ቃል መኖር ስሙም መንፈስንና ሕብረትን ለማጎልበት፤ ግለሰቦችን፣ ማኅበረሰባትንና ዝንቅ የመደብ ጀርባ ያላቸውን ድርጅቶች በጋራ ዓላማ ዙሪያ በአንድነት ለማሰባሰብ ይረዳል። ልዩነቶቻችን እንዳሉ ሆነው ሁላችንም በጋራ ስብዕና የተሳሰርንን ነን የሚለውን ዕሳቤ አበክሮ ልብ ለማሰኘት ያገለግላል።

የስደተኛ ፅኑዕ ተቋቋሚነት

isመሠረታቸው ሲድኒ የሆነ የሕግ ባለሙያና የስደተኞች ሳምንት አምባሳደሮች አንዱ ናቸው። ያደጉት ኢራቅ በአሲሪያን ቤተሰብ ውስጥ ነው። በ1994 አውስትራሊያ መጠለያቸው ከመሆኗ በፊት፤ ጆርዳን፣ ተርክዬና ግሪክ በስደት ኖረዋል።

አቶ ስሌዋ የትውልድ ተዛማች መንፈስ ሁከት ገለል ለማለት በርካታ ዓመታትን እንደሚወስድ፤ ሆኖም ስደተኛች አንዴ የዳግም ሠፈራ ጉዟቸውን ከጀመሩ በኋላ የመፈወስ ዕድል እንዳለ ይናገራሉ።

የ "ፅኑዕ ተቋቋሚነት" መንፈስ ለስደተኞች አንዱና ዋነኛው የፈውስ አካል ነው ይላሉ። "ያም የፈውስ ደረጃ የሚጀምረው እድራቸው አውስትራሊያን ከረገጠ ዕለት አንስቶ ነው" ብለዋል።

ከሌሎች ጋር ከመነጋገር፣ ታሪክዎን ከማጋራት፣ ያላንዳች ጭፍን ጥላቻ በግልፅ ስለዚያ ጉዞ መወያየት ከመቻል ተቀባይነት ይመጣል። ተቀባይነት፣ ዕውቅናንና ከበሬታን ማግኘትም የፈውሱ ሂደት አጋዥ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።
ኦሊቨር ስሌዋ፤ የሕግ ባለሙያና የአውስትራሊያ ስደተኞች ምክር ቤት አምባሳደር
RCOA ambassador, Oliver Slewa
RCOA ambassador, Oliver Slewa Source: Supplied / Supplied by RCOA

'ፊት - ለ - ፊት' ፕሮግራም

በስደተኞች ሳምንትና ከዚያም ባሻገር በአውስትራሊያ ስደተኞች ምክር ቤት የሚከናወኑ በርካታ የተለያዩ ፕሮግራሞችና እንቅስቃሴዎች አሉ።

በስደተኞች ሳምንት ከሚከናወኑት ፕሮግራሞች ውስጥም አንዱ ነው። ይህም በዋስትራሊያ ስደተኞች ምክር ቤት አምባሳደሮችና ተወካዮች አማካይነት የሚካሔድ ገለጣና ሆርሻ ነው።

የስደተኞች ተወካዮች የደኅንነት ዋስትና ጉዞ ግለ ታሪኮቻቸውን ያጋራሉ። ተማሪዎች ስለ ስደተኞች ተሞክሮዎችና ለአውስትራሊያም ስላበረከቷቸው አስተዋፅዖዎች እንዲማሩ ዕድሎችን ይቸራሉ።

ገለጣዎቹ ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ለአስተማሪዎችና ፍላጎቱ ላላቸው ቡድናት ተመጥነው የተሰናዱ ናቸው።

Face-2-Face program workshop
Face-2-Face program workshop Credit: RCOA

የተፈናቃይ ሰዎች ቁጥር ከዕጥፍ በላይ ንሯል

ባለፈው አሠርት ዓመትበጁን 2022 ከ41 ሚሊየን ወደ 103 ሚሊየን ከፍ ብሏል።

ገለጣ መሠረት በ2010 ከ159 አንዱ በግዴታ ተፈናቃይ ከነበረው አሁን ከ95 ሰዎች አንዱ በግዴታ ተፈናቃይ ሆኗል። የሉላዊ ተፈናቃይነት መጠን የውልደት ሕዝብ ቁጥር ጭማሪን አልፎ ሔዷል።

ወ/ሮ ካማራ፤ የአውስትራሊያ ስደተኞች ምክር ቤት የአውስትራሊያ መንግሥት ዓመታዊ የሰብዓዊ ፕሮግራም ቅበላ ቁጥሩን እንዲጨምር እያበረታታ እንዳለ ተናግረዋል።

Share
Published 18 June 2023 7:49pm
Updated 19 June 2023 5:45pm
By Roza Germian, Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS


Share this with family and friends