የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በዩናይትድ ስቴትስ የድጎማ ዕቀባ 'ቅር ተሰኝቻለሁ' አሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ - 19 ጤና ወረርሽኝን በአግባቡ አልተወጣም በሚል አስባብ የአሜሪካንን የገንዘብ ድጋፍ እንደሚገቱ አስታውቀዋል። ውሳኔያቸውን ያሳለፉት በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከሁለት ሚሊየን ባለፈበት ወቅት ነው። ይህንኑ የአቶ ትራምፕን እርምጃ የዓለም መሪዎች በብርቱ የነቀፉት ሲሆን፤ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምም በዩናይትድ ስቴትስ እርምጃ ያዘኑ መሆናቸውን ገልጠዋል።

WHO chief 'regrets' US decision to pull funding

Director General of the World Health Organisation Tedros Adhanom Ghebreyesus Source: AAP

ዩናይትድ ስቴትስ ለዓለም ጤና ድርጅት ለጋስ ከሆኑት አገራት የላቀ ድጎማ የምታደርግ አገር ስትሆን፤ ባለፈው ዓመት በ2019 የጤና ድርጅቱን 15 ፐርሰንት ያህል በጀት ወይም ከ400 ሚሊየን ዶላርስ በላይ ቸራለች።

ይሁንና ፕሬዚደንት ዶናል ትራምፕ ድጎማቸውን አቅበው መያዛቸውን ገልጠዋል።

ውሳኔውም የዓለም መሪዎችን ቅር አሰኝቷል። 

የአውስትራሊያ በጅሮንድ ጆሽ ፍራይደንበርግ በበኩላቸው የዩናይትድ ስቴትስን ውሳኔ እንደሚያከብሩና ሆኖም አውስትራሊያ የራሷን ፈለግ እንደምትከተል ሲገልጡ፤

 

"በቅድሚያ የዓለም ጤና ድርጅት በአካባቢያችን መልካም የጤና ውጤት አስተዋጽ ዖን እያበረከተ እንዳል እየተመለከትን ነው። ተወሰኑት በታዳጊ አገራት የሚያከውኗቸው ትግባራት ጠቃሚ ናቸው። በተባበሩት መንግሥታት በኩል ሉላዊ ድርጅቶችን በመደገፍ ሚናችንን እያበረከትን ነው። ያ ማለት ግና አክፎ - አልፎ ከእነሱ የተለየ አተያዮች የሉንም ማለት አይደለም። ልዩነቶቻችንን እንዲያውቁት እናደርጋለን። የዓለም ጤና ድርጅት የተሻለ ተግባራትን መፈጸም ይቻለዋል፤ ይችላልም። ዓለም አቀፍ አካላትን በመደገፍይ እንቀጥላለን" ብለዋል።    

 

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አንዱ የሰነዘሩት ነቀፌታ  የዓለም ጤና ድርጅት በጣሙን "ቻይና ዘመም" ነው ፤ ቻይና በቫይረሱ ላይ የወሰደችውን አዝጋሚ እርምጃ ደግፏል የሚል ነው።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛኦ ሊጂያን የዓለም ጤና ድርጅት ለመላው ፕላኔት ማለፊያ ተግባራትን እንዲከውን ዩናይትድ ስቴትስ ግዴታዎችዋን ልትወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

 

"ወቅቱ ዓለም እጅጉን አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ ላይ ያለችበት ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ውሳኔ የዓለም ጤና ድርጅትን አቅም ይቀንሳል፤ እንዲሁም ወረርሽኙን ለመፋለም የሚደረገውን ሉላዊ ትብብር ይጎዳል። ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮም እያንዳንዱን አገራት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።  በተለይም አቅመቢስ አገራት ላይ። ዩናይትድ ስቴትስ ግዴታዎችዋን እንድትወጣና ድርጅቱንም በመደገፍ ጸረ ወረርሽኝ ፍልሚያውን በመምራት ዓለም አቀፍ ትብብር እንድታደርግ እናሳስባለን፡፡" 

 

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው በዩናይትድ ስቴትስ እርምጃ ቅሬታ የገባቸው መሆኑን ገልጠዋል።

 

"ዩናይትድ ስቴትስ የዓለም ጤና ድርጅት የረጅም ጊዜ ወዳጅና ለጋስ ናት፤ ይህም ዘላቂ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ድጎማው እንዲቋረጥ በማዘዛቸው ቅሬታ አድሮብናል። በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትና ሕዝብ ድጋፍ የዓለም ጤና ድርጅት ለዓለም አያሌ ደሃና ጉስቁል ሰዎች ጤናቸው የተሻለ እንዲሆን መሥራቱን ይቀጥላል" ብለዋል።    

 

 የዓለም ጤና ድርጅት የአስቸኳይ ጤና ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶ/ር ማይክ ራያን በበኩላቸው ፕሬዚደንት ትራምፕ የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ - 19ኝን አደገኛነት በማሳወቁ ረገድ በጣሙን ዘግይቷል የሚለውን ስሞታቸውን እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል።

 

"በመጀመሪያው ወርሃ ጃኑዋሪ ሳምንታት የዓለም ጤና ድርጅት በታም - በጣም ግልጽ ነበር፡፤ በጃኑዋሪ 5 ለመላው ዓለም አስጠንቅቀናል። በጃኑዋሪ 6 ዩናይትድ ስቴትስን አክሎ የጤና አደጋ ማስጠንቀቂያዎቻቸውን በተጠንቀቅ ደረጃ አድርገዋል። በቀጣዩ ሳምንታትም ውስጥ ለመንግሥታትና የዓለም ሳይንቲስቶች በተከታታይ በመላው ዓለም ተከስተው ስላሉት ሁነቶች ማብራሪያዎችን ሰጥተናል። የቫይረሱ ጃኑዋሪ 7 ታወቀ። ጃኑዋሪ 12 ለመላው ዓለም ሂደቱን  አጋርተናል።"   

 

  የፕሬዚደንት ትራምፕ ተቺዎችም የትራምፕ የዓለም ጤና ድርጅትን የመኮነን እሳቤ መነሾ የዩናይትድ ስቴትስ ባለ ስልጣናት ለቀውሱ የሰጡትን የዘገየ ምላሽ ማለባበሻ አስባብ በመፈለግ እንደሆነ ተናግረዋል። 

የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያና ቅድመ መከላከል በጃኑዋሪ 8 የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያውን የሰጠ ቢሆንም፤ ፕሪዚደንት ትራምፕ ግና ጃኑዋሪ 22 "ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ነው" ብለው እስከተናገሩ ድረስ ቫይረሱን አስመልክቶ ያሉት አልነበረም።  

ጃኑዋሪ 30 የጤና ሚኒስትሩን አሌክስ አዛር የጤና ማስጠንቀቂያ "ሟርተኛ" ብለው አጣጣሉት፡፡

በቀጣዩ ቀን ከቻይና ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በሚመጡ መንገደኞች ላይ የጉዞ እገዳ ጣሉ።

በፌብሪዋሪ 19 ፕሬዚደንቱ ቫይረሱ በኤፕሪል ብን ብሎ ይጠፋል ሲሉ ተናገሩ። ከአምስት ቀናት በኋላ ቫይረሱ "ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በጣሙን በቁጥጥር ስር ነው" አሉ። 

ፌብሪውሪ 27 አቶ ትራምፕ ቫይረሱ "በተአምር እንደሆነ እልም ብሎ ይጠፋል" በማለት ተናገሩ።

በቀጣዩ ቀን ዩናይትድ ስቴትስ በቫይረሱ የመጀመሪያው ሰው ሕይወት መጥፋቱንአስታወቀች።

 የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ እቀባ በድርጅቱ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በመገምገም ሥራዎቹ ሳይቋረጡ ለመቀጠልና ክፍተቱንም ለመሙላት እንዲያስችለው ከሌሎች ሽርካዎቹ ጋር እንደሚሠራ አመላክተዋል። 

 

 በቋንቋዎ ስለ ኮሮናቫይረስ ወቅታዊ ዜናዎችን ለማግኘት sbs.com.au/coronavirus ድረ - ገጻችንን ይጎብኙ።


Share

Published

Updated

By Allan Lee
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends