ጄኔራል ታደሰ ወረደና ጄኔራል ፃድቃን ወልደ ተንሳይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው ተሾሙ

አዲሱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ የተዋቀረው ከሕወሓት፣ ከትግራይ ኃይሎች፣ ከምሁራንና ከብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ (ባይቶና) ፖለቲካ ፓርቲ የተውጣጡ አባላትን በማካተተት ሲሆን፤ የካቢኔው 51 በመቶ ቦታ በሕወሓት ተይዟል፤ ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ ሁለት ቢሮዎችን በኃላፊነት የመምራት ዕድል አግኝቷል።

General Tadesse Worede.jpg

General Tadesse Worede in Nairobi on November 12, 2022. Credit: YASUYOSHI CHIBA/AFP via Getty Images

አዲስ በተቋቋመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እና ጀነራል ፃድቃን ገብረተንሳይ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ተደርገው ተሾመዋል።

ይኸው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 27 አባላት ያሉትን ካቢኔ ይፋ ባደረገበት ወቅት ተገልጿል።

በአዲሱ ካቢኔ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ሆነው ሲሾሙ፣ ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ ደግሞ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ሆነዋል።

ሹመቱ በመቐለ ከተማ ይፋ ሲደረግ የክልሉን መንግስት ሲመራ የነበረው የቀድሞ ካቢኔ፤ የአስፈጻሚነት ስልጣኑን በጊዜያዊ አስተዳደሩ ለተቋቋመው አዲሱ ካቢኔ አስረክቧል።

አዲሱ ካቢኔ የተዋቀረው ከህወሓት፣ ከትግራይ ኃይሎች፣ ከምሁራን እና ከብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ (ባይቶና) ፖለቲካ ፓርቲ የተውጣጡ አባላትን በማካተተት ነው። የካቢኔው 51 በመቶ ቦታ የተያዘው በህወሓት ሲሆን፤ ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ ሁለት ቢሮዎችን በኃላፊነት የመምራት ዕድል አግኝቷል።

ከትግራይ ኃይሎች በካቢኔው ውስጥ የኃላፊነት ቦታ ያገኙት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ብርጋዴር ጄነራል ተኽላይ አሸብር፣ ሌተናን ጄነራል ፍሰሃ ኪዳኑ እና ሜጀር ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ ናቸው።

Share

Published

Updated

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends