ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ መጤዎች የሚሠሩበት ብሩክሊን - ሜልበርን ካለው ሲዳር ሥጋዎች ፋብሪካ ጋር በተገናኘ ትናንት ማምሻውን አራት ሰዎች በተጨማሪ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን አክሎ 49 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸው ታውቋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በእርድ ሥጋ ማዘጋጃው የቫይረሱ መከሰት የታወቀው ኤፕሪል 2 ቢሆንም፤ ያ አሁን ተከስቶ ካለው የወረርሽኙ መዛመት ጋር ተያያዥነት እንዳለው በባለ ሥልጣናት ዘንድ አልታመነበትም።
ሆኖም ቫይረሱ ለሁለተኛ ጊዜ ኤፕሪል 24 ተከስቷል።
እንዲያም ሆኖ እስከ ኤፕሪል 29 ድረስ በዲፓርትመንቱ በኩል ሁሉንም ሠራተኞች እንዲመረመሩ ማድረጉን ጨምሮ ታካይ እርምጃዎች አልተወሰዱም።
ማክሰኞ ዕለት ቪክቶሪያ ውስጥ 17 ሰዎች በኮቪድ - 19 መያዛቸው ሲገለጥ 11ዱ የሲዳር ሥጋዎች ፋብሪካ ሠራተኞች ናቸው።
ከሜልበርን እርድ ሥጋ ማዘጋጃ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ 11 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቁ

ከሜልበርን እርድ ሥጋ ማዘጋጃ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ 11 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቁ
የቪክቶሪያ ዋና የጤና ኃላፊ ፕሮፌሰር ብሬት ሳቶን ቫይረሱ ተስፋፊነቱ ቢያዘግምም አለመክሰሙን ሲያስገነዝቡ፤
"በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መጨመር ዳግም ልብ የሚያሰኘን ምንም እንኳ የቫይረሱ ተዛማችነት እያሽቆለቆለ ቢሔድም፤ ከኮቪድ - 19 ጋር የምናደርገው ፍልሚያ ለፍጻሜ የተቃረበ አለመሆኑን ነው" ብለዋል።
ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ በጤና ጠበብት ምክረ ሃሳብ መሠረት እስከ ሜይ 11 የማኅበራዊ ርቀት ገደቦች ጸንተው እንዲቆዩ ባሳለፉት ውሳኔ ጸንተዋል።

Victorian Premier Daniel Andrews. Source: AAP
በአንድ የቪክቶሪያ እርድ ሥጋ ማዘጋጃ በተከሰተው ኮቪድ - 19 ሠራተኞቹ ተያዙ

በአንድ የቪክቶሪያ እርድ ሥጋ ማዘጋጃ በተከሰተው ኮቪድ - 19 ሠራተኞቹ ተያዙ
የብሔራዊ ካቢኔው ተጥለው ያሉ ገደቦችን ለማላላትና ብሔራዊ መርሃ ግብሮችን ለመዘረጋት የፊታችን ዓርብ ይታደማል።