"በኢትዮጵያዊነቴ ኮርቻለሁ፤በሕይወት እያለሁ ይህን ክብር በማየቴ አመሰግናለሁ"ለማ ክብረት "በዝግጅቱ ኢትዮጵያዊነትን አይቼበታለሁ"የሺሐረግ ግርማ

Lemma and Yeshihareg.png

Yeshihareg Girma (L), Lemma Kibret (C) and their son (R). Credit: SBS Amharic

ከአምስት ዓለም አቀፍ ፍፁም ቅጣት ምቶች አራቱን በማዳን የግብ ጠባቂ ሬኮርድ ያስመዘገበውና በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ኢትዮጵያ ሞሪሽየስን ለማሸነፍ እንድትበቃ ላስቻለው አንጋፋና ዝነኛው ለማ ክብረት ቅዳሜ ሰኔ 1 ቀን 2016 በሜልበርን - አውስትራሊያ የተካሔደው የዕውቅናና ምስጋና ምሽት ዝግጅት ተጠናቅቋል። ስኬቱም በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ዘንድ የ"ይበልና ይቀጥል" ስሜትን አሳድሯል።


አንኳሮች
  • ልዩ የዕውቅናና ምስጋና ምሽት
  • የማኅበረሰብ አባላትና አዘጋጆች አተያዮች
  • የምስጋና ቃሎች

Share