አንኳሮች
- ማርሻል አርት እና ሴቶች
- ማርሻል አርት አካልን እና ጭንቅላትን የሚያንጽ አርት ነው
- ከኳታር የተገኙ ትርፋቶች
ኢትዮጵያ ጌታቸው የቀድሞ የኳታር በሄራው ቡድን የማርሻል አርት እና ቴኳንዶ አሰልጣኝ ስትሆን ወደዚህ ሙያ የተቀላቀለችው ገና የዘጠኝ አመት ታዳጊ በሆነችበት እድሜዋ ነበር ።
![አሰልጣኝ ኢትዮጵያ ከሰልጣ](https://images.sbs.com.au/47/ca/2c2402284fe2969d43eb80992e10/1c7664c4-3c1e-4937-9b48-a061ee144079.jpeg?imwidth=1280)
E Getachew
![አሰልጣኝ ኢትዮጵ ከኳታር ቴኳንዶ ብሄራዊ ቡድን አባላት ጋር](https://images.sbs.com.au/1f/07/1050c7194304b86881440181914d/63c46f92-73b2-4dcd-982f-c38b6fc3e620.jpeg?imwidth=1280)
E, Getachew.
ኢትዮጵያ የባህር ማዶ ህይወቷን በዱባይ ብትጀምርም ሙያዋን በተግባር እንድታውል በሯን ከፍታ የተቀበለቻት አገር ግን ኳታር ነበርች። እንደ ኢትዮጵያ አባባልም የኳታር መንግስት ለስፓርት ከሚሰጠው ከፍተኛ ትኩረት እና እገዛ የተነሳ እሷም የአገሪቱን የብሄራዊ ቡድን በማርሻል አርት እና ቴኳንዶ ለማሰልጠን እድሉ አግኝታ ቡድኑን ከውጤት ጋር ለ11 አመታት ያህል አሰልጥናለች።
![2DE3803C-6B63-4230-A21B-EC6C3E301387.jpeg](https://images.sbs.com.au/03/92/ce1316ea4b1f925e68a04b3f2dce/5c940e01-82f7-46a7-887d-1a145d588451.jpeg?imwidth=1280)
E, Getachew